በስላብ እና ቢም የብረት ስራ (Slab & Beam Rebar Reinforcement) ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ… — Ethio Construction Engineering — TG.ME

👉በስላብ እና ቢም የብረት ስራ (Slab & Beam Rebar Reinforcement) ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ የጥራት ቁጥጥሮች!

🏛​በምስሉ ላይ እንደሚታየው የህንፃው የስላብ (Concrete Slab) እና የቢም (Beam) የብረት ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ለኮንክሪት ሙሌት ዝግጁ እየሆነ ይገኛል።

📌 በሳይት ደረጃ ኢንጂነሩ ኮንክሪት ከመፈሰሱ በፊት ሊያረጋግጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

1️⃣ የብረት መጠንና ክፍተት (Rebar Size & Spacing): በስትራክቸራል ዲዛይኑ (Structural Drawing) መሠረት ዋና ዋና የብረት መጠኖች (Main Bars)፣ የማደሪያዎች (Stirrups/Ties) ክፍተት እና የላፕ ርዝመት (Lap Length) በትክክል መሰራታቸውን ማረጋገጥ።

2️⃣ የኮንክሪት ከቨር ስፔሰር (Concrete Cover Blocks): በስላብ እና ቢም ብረቶች ስር ተገቢው የከቨር ስፔሰር መቀመጡን ማረጋገጥ፤ ካልሆነ ብረቱ ከውጭ ታይቶ የመዝገት (Corrosion) አደጋ ይጋረጣል።

3️⃣ የፎርምወርክ እና የሾሪንግ ጥንካሬ (Formwork & Shoring Stability): ከስር የተደረጉት ማስደገፊያዎች (Props) እና የፕላይዉድ/የእንጨት ፎርምወርኮች የኮንክሪቱን እና የሰራተኞቹን ክብደት የመሸከም አቅም እንዳላቸው ማረጋገጥ።

4️⃣ የፅዳት እና የፍርስራሽ ቁጥጥር (Site Cleanliness):ኮንክሪት ከመፈሰሱ በፊት በስላቡ እና በቢሙ ውስጥ ያሉ የእንጨት፣ የብረትና የቆሻሻ ፍርስራሾችን በደንብ ማጽዳት።

🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
❤2
August 31, 2026 1K 10