በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት በየዓመቱ 100 ሺህ የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ ​የአዲስ አበባ ከተማ… — Ethio Construction Engineering — TG.ME

​በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ 5 ዓመታት በየዓመቱ 100 ሺህ የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ
​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባለፉት አምስት ዓመታት ባከናወናቸው ሁለገብ የቤት ልማት ስራዎች ከ496 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት መቻሉን አስታወቀ፡፡

​ቢሮው በመጪዎቹ አምስት ዓመታትም በየዓመቱ 100 ሺህ ቤቶችን ገንብቶ ለቤት ፈላጊዎቹ ለማቅረብ እቅድ ይዞ ወደ ስራ መግባቱን የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ገልጸዋል።

​የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በዘላቂነት ለመመለስ በተከናወኑ ሁለገብ ስራዎች የቤት ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም ሰፊ ጥረት መደረጉን የጠቆሙት ኃላፊዋ፣ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች የሚከተሉት ናቸው፡

​የተከናወኑ የግንባታ ውጤቶች፦ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወደ 496 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተዋል።

​የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ፦ የመንግስትን ጥረት ብቻ ሳይገድብ፤ የግሉን ዘርፍና ሪል ስቴት አልሚዎችን በማሳተፍ ምቹ ሁኔታዎችና መደላደሎች ተፈጥረዋል።

​የተጠቃሚዎች ማዕቀፍ፦ ማህበራትን በማደራጀት፣ የ40/60 እና የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ጠባቂዎችን፣ የመንግስት ሰራተኞችን እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማቀፍ ወደ ቤት ልማት እንዲገቡ ተደርጓል።

​በመንግስትና በግል አጋርነት (PPP) የተከናወኑ አዳዲስ የልማት ሞዳሊቲዎች ውጤት ማፍራታቸውን የገለጹት ወይዘሮ ቅድስት፣ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የነዋሪዎችን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የመጪዎቹ አምስት ዓመታት ዋና ዋና ስትራቴጂዎችና እቅዶች መካከል አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል።

@etconp
❤3👍2
August 31, 2026 1.4K 1