👉የኮለን ፎርምወርክ ቼክሊስት[Elements of good Column formwork finish]
1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/
የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ነው።
2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/
ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን
3.አቀባዊ ሊኛ/ቱምቢ/Vertical alignment/
የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን
4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/
ኮለምኑ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው መሆኑን
5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/
የኮለኑ ወርድና ስፋት በዲዛይኑ መሰረት መሰራቱን ማረጋገጥ።
6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/
አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን
7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/
ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ
8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Design cover/
በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።
@etconp

16August 27, 2026 3K 27