በኔፓል እና በቻይናዋ ቲቤት ወሰን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ የደረሰው ድንገት ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የገደላቸው ሰዎች ብዛት ወደ 900 በላይ ደረሰ፡፡
በአደጋው የደረሱበት የጠፋው ሰዎች ብዛት ከ4 ሺህ 300 እንደማያንስ መነገሩን ቢቢሲ ፅፏል፡፡
የደረሱበት ከጠፋው መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በሀይል ማመንጫ ዋሻ ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰራተኞች ናቸው ተብሏል፡፡
በቻይናዋ ቲቤት አደጋው የገደላቸው ሰዎች ብዛት 16 መደረሱን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
በዚያ ከ540 በላይ ሰዎች አሁንም ድረስ የደረሱበት እንዳልታወቀ ተጠቅሷል፡፡
በኔፓል አሁንም የሚጥለው ዶፍ ዝናብ የረድኤት ጥረቱን በጣሙን አዳጋች እያደረገው መምጣቱ ተሰምቷል፡፡
ለእርዳታ የተላኩ ብዙ መኪኖች በመንገዱ በጎርፍ በጎርፍ መጠራረግ ምክንያት መተላለፊያ አጥተው በማጥ ውስጥ መያዛቸው ሁኔታውን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል ተብሏል፡፡











