K.k.s.c Wereda 03 karakore gudgnt: post #3841 — TG.ME

የ2019 የትምህርት ዘመን የአዳሪ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ቅበላ ውድድር   ማስታወቂያ (ሀምሌ 9 /2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ የገላን የወንዶች እና የእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በየዓመቱ 7ኛ እና 9ኛ ክፍልን በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በማወዳደር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡   በ2018 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተምረው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች ለወንድ ተማሪ  በገላን የወንዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም ለሴት ተማሪ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አወዳድሮ በ2019 ዓ.ም ቅበላ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለመግባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 1.   በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማስተማሪያ ቋንቋ በአማርኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ በመማር ላይ የነበረ/ች፤ 2.   በ2018 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ /Average/ ውጤት 80% እና በላይ፤ እንዲሁም በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ/Average/ ውጤት 80%ና በላይ ያስመዘገበ/ች 3.   በ2018 ዓ.ም ከሚማሩበት ትምህርት ቤት ምንም ዓይነት የስነ-ምግባር ችግር እንደሌለባቸው  ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤ 4.   በትምህርት ቤቱ በልዩ ልዩ ተጓዳኝ ክበባት በንቃት ተሳታፊ የሆነ/ነች፤ 5.   7ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች የ5ኛ ክፍል ውጤት አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ሆኖ በሒሳብ ትምህርት ዓይነት አማካ

July 23, 2026 393