የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር የውጭ… — Ethiopian Police University Official Page — TG.ME

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር የውጭ ቫሊዴሽን (External Validation) ወርክሾፕ አካሄደ
***
​ነሐሴ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
​የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር የውጭ ቫሊዴሽን (External Validation) ወርክሾፕ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

​በወርክሾፑ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ታምራት ሙሉጌታ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሀገሪቱን የፍትሕ ስርዓት ለማዘመን የተቋማት ቅንጅትና የዕውቀት ሽግግር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለፖሊስ ትምህርትና ስልጠና የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት መሰረት በማድረግ መሰል ሙያዊ ትብብሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

​በሌላ በኩል የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል የኑስ ሙሉ በበኩላቸው "የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለማረሚያ ኮሌጅ እያደረገ ያለው ድጋፍ የተቋማቱን የጋራ እድገት እቅድ የሚያጠናክር ነው" ብለዋል።

በተጨማሪም ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያከበረ፣ በምርምርና ዕውቀት ላይ የተመሰረተ የማረም ስርዓት ለመገንባት ከአጋር ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
👍63❤37🔥4✍3👏2
August 10, 2026 9.2K