ገብርኤል ገብርኤል መላከ ራማ(፪) ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምፅህን እንስማ(፪) ትንቢቱ ሲፈፀም ዘመኑ ሲያበቃ… — ያሬዳውያን — TG.ME

ገብርኤል ገብርኤል መላከ ራማ(፪) ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምፅህን እንስማ(፪) ትንቢቱ ሲፈፀም ዘመኑ ሲያበቃ ከቀናት ሳትዘገይ ሳይጎድል ደቂቃ ወደ ድንግል መጠህ ደስታን አበሰርክ የአምላክን ሰው መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪) ከውሃ እና ከእሳት ከሞት አመለጡ በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ ምንም ቦታ የለው ሞትና መከራ(፪) የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና ዛሬም ላገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪) አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ ስላንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ እሳት ነህ ገብርኤል ነበልባል አስወጋጅ የአምላክን መወለድ ለአለም የምታውጅ(፪)            

❤41🥰5
August 25, 2026 12.2K 7 38