በአለም አቀፍ ውጥረቶች ምክንያት በአፍሪካ የሀገር ውስጥ Cloud እና Sovereign AI ፍላጎት ጨመረ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣው የጂኦፖለቲካ ውጥረት እና በውጭ ሀገር ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ላይ ያለው ጥገኝነት በአፍሪካ የሀገር ውስጥ Cloud እና Sovereign AI ፍላጎትን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገው ይገኛል። እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ ሀገራት ተቋማት መረጃዎቻቸው እና የ AI ሞዴሎቻቸው በውጭ አገልጋዮች ላይ መከማቸታቸው ለአገልግሎት መቋረጥ እና ለደህንነት ስጋት ያጋልጠናል በሚል አሰራራቸውን እየገመገሙ ነው። በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት 45 በመቶ የሚሆኑ የአፍሪካ ተቋማት በጂኦፖለቲካዊ ለውጦች ምክንያት የሳይበር እና የ Cloud ስትራቴጂያቸውን እንደገና ለማዋቀር ተገደዋል። እንደ Altron ያሉ ኩባንያዎችም በሀገር ውስጥ ገንዘብ የሚሰሉ የ Sovereign AI እና የ Cloud አገልግሎቶችን ማቅረብ ጀምረዋል። የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት በበኩሉ አህጉሪቱ በውጭ AI አቅራቢዎች ላይ ያላት ከፍተኛ ጥገኝነት የጤና፣ የፋይናንስ እና የባዮሜትሪክ መረጃዎችን ባለቤትነት አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠነቅቋል። አህጉሪቱ በራሷ መሰረተ ልማት ሳትገነባ ቴክኖሎጂውን ብቻ በህግ ለመቆጣጠር መሞከሯ ውጤታማ እንደማያደርጋት ተገልጿል። በመሆኑም የውጭ የቴክኖሎጂ የበላይነትን ለመቀነስ እና የመረጃ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥ የ Cloud እና AI መሰረተ ልማቶችን መገንባት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል። 🔗 ITWeb Africa #Cloud #AI #Africa
ITWebFear of foreign shutdowns drives local cloud demandGeopolitical tensions drive demand for local cloud hosting and sovereign AI, as businesses seek to reduce reliance on foreign tech providers.በአለም አቀፍ ውጥረቶች ምክንያት በአፍሪካ የሀገር ውስጥ Cloud እና Sovereign AI ፍላጎት ጨመረ… — ENX (Tech) — TG.ME
October 26, 2026 9