CANAL+ የ MultiChoice ገቢ በመቀነሱ በደቡብ አፍሪካ የማሻሻያ እርምጃዎችን እያወሰደ ነው የፈረንሳዩ የሜዲያ ግዙፍ ኩባንያ CANAL+ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን MultiChoiceን አፈጻጸም ለማሻሻል እና ከገጠመው የገቢ ቅናሽ ለማውጣት የ DStv ፓኬጆችን የማሻሻል እና አዳዲስ ይዘቶችን የማቅረብ ሥራ እያከናወነ ይገኛል። እስከ መስከረም ባሉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የ MultiChoice አጠቃላይ ገቢ በ 3% ገደማ ቀንሶ 1.81 ቢሊዮን ዩሮ (2.03 ቢሊዮን USD) ደርሷል። ይህ የገቢ ቅናሽ በዋናነት በደቡብ አፍሪካ ከደንበኞች የሚሰበሰበው የደንበኝነት ምዝገባ ገቢ በመቀነሱ የተከሰተ ሲሆን፣ ኩባንያው በመስከረም ወር ደንበኞችን ለመሳብ ቀላል እና የተሻለ ዋጋ ያላቸውን የ DStv አገልግሎት አማራጮች ማስተዋወቅ ጀምሯል። ይህ የማሻሻያ እርምጃ ኩባንያው MultiChoiceን ከተቆጣጠረ በኋላ እያደረገ ያለው የለውጥ አካል ሲሆን፣ የኦንላይን ስትሪሚንግ አገልግሎት የሆነውን Showmax በቅርቡ ማቆሙን ተከተሎ የመጣ ነው። CANAL+ በፈረንሳይኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የ 10.2% የገቢ እድገት ያስመዘገበ ቢሆንም፣ የ MultiChoice ድርሻ ግን ቅናሽ አሳይቷል። ኩባንያው በአህጉሪቱ ያለውን የገበያ ድርሻ ለማስጠበቅ ከ 2027 እስከ 2031 የሚከናወኑ የ UEFA የእግር ኳስ ውድድሮች እና የ 2027 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) የስርጭት መብቶችን ማግኘቱን ገልጿል። 🔗 TechCabal #CANAL #MultiChoice #Media
TechCabalCANAL+: Africa growth slows in biggest Pay-TV marketCANAL+ faces a South African test as MultiChoice revenue falls 3%, prompting new DStv packages and stronger content to revive growth.CANAL+ የ MultiChoice ገቢ በመቀነሱ በደቡብ አፍሪካ የማሻሻያ እርምጃዎችን እያወሰደ ነው የፈረንሳዩ… — ENX (Tech) — TG.ME
October 22, 2026 8