Safaricom በኬንያ ለ M-PESA ተጠቃሚዎች የመረጃ ደህንነትን የሚያስጠብቅ M-PESA Jumbe አቀረበ
Safaricom በኬንያ የ M-PESA ተጠቃሚዎች ክፍያ ሲፈጽሙ የከፈሉበትን ማስረጃ በሚያሳዩበት ወቅት ሙሉ ስማቸውን፣ የስልክ ቁጥራቸውን እና የሂሳብ ቀሪያቸውን ለሌሎች እንዳይገልጡ የሚያደርግ M-PESA Jumbe የተሰኘ አዲስ አገልግሎት ይፋ አደረገ። ይህ አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች JumbeID በተሰኘ ልዩ ምህፃረ-ቃል መጠሪያ ክፍያን ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያደርግ ነው። በተጨማሪም የ Lipa na M-PESA እና Pochi la Biashara ነጋዴዎች የክፍያ ማሳወቂያዎች ለሰራተኞቻቸው ስልክ በቀጥታ እንዲደርሱ እስከ 50 የሚደርሱ ተጨማሪ ተቀባዮችን ማካተት እንዲችሉ ዕድል ይሰጣል።
ይህ አሰራር በኬንያ ባሉ ሬስቶራንቶች፣ ነዳጅ ማደያዎች እና ሱቆች ውስጥ የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ለማሳየት በሚደረግበት ወቅት የሚፈጠረውን የመረጃ መጋለጥ እና የእንግልት ችግር ይቀርፋል። የንግድ ድርጅት ባለቤቶች በቦታው በሌሉበት ጊዜም ሰራተኞች የባለቤቱን ስልክ ሳይጠብቁ ወይም የድርጅቱን የ M-PESA ሚስጥራዊ ቁጥርና የሂሳብ መጠን ማየት ሳያስፈልጋቸው ክፍያዎችን በራሳቸው ስልክ ወዲያውኑ ማረጋገጥ ይችላሉ። አገልግሎቱን በ *234# የአጭር ቁጥር መደወያ በኩል ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ በላቁ ስማርትፎኖች እንዲሁም በመደበኛ ስልኮች ላይ በ SMS እና USSD በኩል የሚሰራ ነው።
🔗 TechTrends KE
#MPesa #Safaricom #Fintech

TechTrendsKE
Safaricom rolls out M-PESA Jumbe to make payment confirmation more private
M-PESA Jumbe lets customers share proof of payment without exposing their full name, phone number or balance. Eligible merchants can also send payment alerts to authorised staff.
October 21, 2026 13