Kaspersky የ Gen Z ትውልድ ለሳይበር ጥቃት የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገለፀ የሳይበር ደህንነት…

Kaspersky የ Gen Z ትውልድ ለሳይበር ጥቃት የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገለፀ

የሳይበር ደህንነት ኩባንያው Kaspersky ባካሄደው ዓለም አቀፍ ጥናት፣ የ Gen Z ትውልድ በኢንተርኔት ላይ ከፍተኛ ጊዜ የሚያሳልፍ ቢሆንም ለሳይበር ጥቃቶች በስፋት የመጋለጥ እድል እንዳለው ተገለፀ። በጥናቱ ከተሳተፉት 7,200 ሰዎች መካከል 52% የሚሆኑት የመሳሪያ ወይም የኦንላይን አካውንት ጥቃት እንደደረሰባቸው የተናገሩ ሲሆን፣ 17% የሚሆኑት የሶሻል ሚዲያ እና 12% የሚሆኑት ደግሞ የኦንላይን ጨዋታ አካውንቶቻቸው ተጠልፈውባቸዋል። በተጨማሪም 67% የሚሆኑት ስማርትፎንን ዋነኛ የኢንተርኔት መጠቀሚያ የሚያደርጉ ቢሆንም፣ በስልካቸው ላይ የሞባይል አንቲቫይረስ ሶፍትዌር የሚጠቀሙት 27% ብቻ እንደሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል።

ይህ ግኝት የወጣቶቹ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በራስ መተማመን እና እራሳቸውን ከሳይበር ስጋቶች የመጠበቅ አቅማቸው መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ያሳያል። እንዲሁም በጥናቱ ከተካተቱት መካከል 38% የሚሆኑት በስልካቸው ላይ ያሉ ፎቶዎችን እና ሰነዶችን በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ ቢገልጹም፣ መረጃዎቻቸውን አዘውትረው ባክአፕ የሚያደርጉት 28% ብቻ ናቸው። Kaspersky ወጣቶች ጠንካራ የይለፍ ቃላትን እንዲጠቀሙ እና የደህንነት ሶፍትዌሮችን እንዲጭኑ ከመመከሩም በላይ፣ የፊሺንግ እና የማጭበርበር ሙከራዎችን መለየት የሚያስችል Case 404 የተሰኘ የኦንላይን ጨዋታ ይፋ አድርጓል።

🔗 TechTrends KE
#Cybersecurity #Kaspersky #GenZ
TechTrendsKE
Kaspersky research exposes gaps in Gen Z’s everyday cybersecurity habits
More than half of surveyed Gen Z respondents reported cyberattack experiences, while mobile antivirus use and regular smartphone backups remain uncommon.
October 21, 2026 12