የግብፅ የፋይንቴክ ኩባንያ MNT-Halan በይፋዊ የአክሲዮን ሽያጭ 150 ሚሊዮን USD ሰበሰበ
የግብፅ የመጀመሪያው ዩኒኮርን MNT-Halan በግብፅ አክሲዮን ገበያ ያካሄደውን የ150 ሚሊዮን USD ይፋዊ የአክሲዮን ሽያጭ (IPO) በመጨረስ የመጀመሪያ ቀን የንግድ እንቅስቃሴው የአክሲዮን ዋጋው በ18 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ኩባንያው 320 ሚሊዮን አክሲዮኖችን የሸጠ ሲሆን ይህም 7.84 ቢሊዮን የግብፅ ፓውንድ (144.1 ሚሊዮን USD) ገቢ አስገኝቷል። ይህ ሽያጭ የMNT-Halan የግብፅ የንግድ ክንፍ 20 በመቶ ድርሻ የሚወክል ሲሆን፣ የሃገር ውስጥ ክፍሉን ዋጋ ወደ 745 ሚሊዮን USD ያደርሰዋል። የኢንቨስተሮች ፍላጎት ከፍተኛ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የድርጅት ኢንቨስተሮች ከተመደበላቸው በላይ በ11.2 እጥፍ እንዲሁም ግለሰቦች በ43.6 እጥፍ አክሲዮኖችን ለመግዛት ጠይቀዋል።
በ2018 እ.ኤ.አ. በMounir Nakhla የተመሰረተው MNT-Halan ለማይክሮፋይናንስ፣ ለአነስተኛ ንግዶች እና ለዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች ትኩረት በመስጠት ፈጣን እድገት አስመዝግቧል። ኩባንያው ከግብፅ ውጪ ወደ ፓኪስታን እና ቱርክ የተስፋፋ ቢሆንም፣ አሁን የተካሄደው የአክሲዮን ሽያጭ የግብፅን የንግድ እንቅስቃሴ ብቻ የሚሸፍን ነው። ይህ ክስተት ትርፋማ የሆኑ የአፍሪካ የፋይንቴክ ኩባንያዎች በይፋዊ የአክሲዮን ገበያዎች ላይ የካፒታል አማራጮችን ለመጠቀም ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው፤ እንዲሁም የገበያውን ዝግጁነት ይፈትናል።
🔗 Benjamindada
#Fintech #Egypt #IPO

Condia
MNT-Halan shares jump 18% after $150M Egypt IPO
Egypt’s fintech unicorn MNT-Halan saw shares rise 18% on debut after its $150 million IPO attracted strong investor demand.
October 20, 2026 15