እ.ኤ.አ. በ2029 የ AI ኤጀንቶች ቁጥር ከሰዎች በይነመረብ ተጠቃሚዎች ይበልጣል ተባለ
በሚቀጥሉት ከሁለት እስከ ሶስት ዓመታት ውስጥ በበይነመረብ ላይ የሚንቀሳቀሱ የ AI ኤጀንቶች (AI agents) ቁጥር ከሰዎች በይነመረብ ተጠቃሚዎች በላይ እንደሚሆን የ Convergence Partners ተመስራችና የ Digital Council Africa ሊቀመንበር Dr Andile Ngcaba ገለጹ። እንደ ባለሙያው ገለፃ እ.ኤ.አ. በ2030 በበይነመረብ ላይ የሚንቀሳቀሱ በህይወት ያሉ ሰዎች ቁጥር ከ AI ኤጀንቶች አጠቃላይ ቁጥር አንፃር በጣም አነስተኛ ይሆናል። እነዚህ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኤጀንቶች ከተለመዱት ቻትቦቶች አልፈው የተለያዩ ዲጂታል መሣሪያዎችን የመጠቀምና ባለብዙ ደረጃ ተግባራትን በራሳቸው የማከናወን አቅማቸውን እያሳደጉ ይገኛሉ።
ይህ ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ኩባንያዎችና መንግስታት ለ AI የሚሰጡትን ትኩረትና የቁጥጥር ስርዓት እንደገና እንዲፈትሹ እያስገደደ ነው። Dr Andile Ngcaba እንደገለጹት የአፍሪካ ሀገራት የፈጠራ ስራዎችን ከማገደብ ይልቅ የቴክኖሎጂ አበልፃጊዎችን መደገፍ አለባቸው። እንደ አውሮፓ ህብረት ያሉ ጥብቅ የህግ ማዕቀፎችን በቀጥታ ከመቅዳት ይልቅ ለአህጉሪቱ ተስማሚና ተለዋዋጭ አሰራሮችን መከተል እንደሚገባና የ AI ስጋቶችን ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
🔗 ITWeb Africa
#AI #Africa #Tech
ITWeb
AI agents to outnumber humans online by 2029
Rapid innovation forces businesses and governments to rethink how they approach the emerging tech, says prominent IT figure Andile Ngcaba.

October 20, 2026 12