መረጃ ይዳኘን ክፍል ①②
[ሑጀቱል ኢስላም አል-ገዛልይ]
ስማቸው ከቀደምት ግዜያት ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ ሳይጠለሽ በክፉም ሳይደበዝዝ በበጎ ከሚታወሱ አኢማዎች መሀከል ሑጀቱል-ኢስላም የሚሰኙት ስመ ገናናው ኣቡ-ሓሚድ አል-ገዛልይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይገኙበታል።እኚህ ታላቅ ሰው የሰለፍን ዘመን አልፈው ኸለፍ ከሚሰኙት የእውቀት ሊሂቃን የሚመደቡ ሲሆን፤በመዝሃብ ደረጃ የሻፊዒይን፣ በዒልም ደረጃ አል-ሙጅተሂድ ፊል መዝሀብ የተሰኙ በዓቂዳ መንገድ አ'ሽዓርይነትን የተላበሱ ታላቅ የኢስላማዊ እውቀት ምሁር ናቸው።
አል-ኢማሙ ኣል-ገዛልይ 450-505 አመተ ሂጅራ የቆዩ ሲሆን ከመሻይኾቻቸው መሀከል አቡል-መዓሊይ አል-ጁወይንይ አንዱ ሲሆኑ ከተማሪያቸው ውስጥ ደግም ታላቁ ወልይ ኣቡበክር ብኑል ዓረብይ ይገኙበታል።
እኚህ ታላቅ የእውቀት ሰው ከዓቂዳ ዘርፍ አንስቶ እስከ ፊቅሂ የተዋጣላቸው የኢልም ባልተቤት መሆናቸው እብለት የሌለው ፍንትው ያለ እውነት ነው።ከሰነዷቸው ኪታቦች መሀከልም ኢልጃሙል ዓዋም ፊይ ዒልሚል ከላም፣ አል-ሙስተስፋ፣ ኢ'ሕያእ ሌሎችም ጥቂት ማይባሉ እውቀታቸውን በይፋ የሚያስተጋቡ መፅሀፎችን ለኡማው አበርክተዋል።
እንዲህ ያሉ ታዋቂ ሊሂቃን ምእመኑ ኮርቶ ወደነርሱ በመጠጋት ንግግራቸውን በማስረጃነት ቀን ከሌት መፅሀፍቶቻቸውን በመያዝ እንደሚደጋግመው ሁሉ፤ በተቃራኒው የእስልምና ጠላት የሆኑ ሰዎች የነዚህ ሊሂቃን እውቅናን በመጠቀም ጥለው በሄዱት በጎ አሻራዎች ላይ የራሳቸውን መርዝ ቀስ በቀስ በቀለሙ እንዲሁ በአይነቱ አመሳስለው ለኡማው በመስጠት ለምእመኑ የእፍረት ካባ ለማከናነብ መጣር ከጀመሩም ዋል አደር ያሉም አልጠፉም።
በዛሬው ርዕሴ ኣቡ-ሐሚድ አል-ገዛልይ (ሑጀቱል ኢስላም) በአህሉል ቢድዓዎች ላይ ከነርሱ ውስጥም ሙጀሲማ የሚሰኙት አንጃዎች ላይ ያላቸው ፅኑ አቋም ምን ይመስል ነበር የሚለውን ኪታቦቻቸውን እያስደገፍኩ አጠር ባለ መልኩ በማስረጃ የማቀርብ ይሆናል።
¤ በመጀመርያ ሑጀቱል-ኢስላም ኣቡ'ሓሚድ አል-ገዛልይ ኢ'ልጃሙል ዓዋም ፊይ ዒልሚል ከላም በተሰኘ ኪታባቸው ላይ ገፅ 96 ላይ እንዲህ ሲሉ ያሰፈሩትን እንመልከት፦
* قال في إلجام العوام 〔وأن من عبد جسماً فقد عبد صنماً سواء كان الجسم صغيراً أو كبيراً، قبيحاً أو جميلاً، سافلاً أو عالياً على الأرض أو على العرش، فكان نفي الجسمية ونفي لوازمها معلوماً لكافتهم على الضرورة بإعلام رسول الله صلى الله عليه وسلم والمبالغة على التنزيه لقوله: لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ ) سورة الشورى: (۱۱〕
① [“ፈጣሪ ብሎ ያሰበው "አካል" ትንሽ አልያ ትልቅ፣አስጠሊታ አልያ ቆንጆ፣ከላይ ያለ ወይም ከታች ፣በምድር አልያ ከዓርሽ በላይ ብሎ ብያስበውም፤ አካልን የተገዛ #ጣኦትን እንደተገዛ ነው። አካልን ሆነ አካልን የሚያሲዙ ነገራቶች ከአሏህ የራቁ እንደሆኑ ሁሉ በሚጋራው መልኩ በነብዩ አድራሺነት እንዲሁ አሏህን በሚያጠሩ አናቅፅቶች የተሰራጨ ሲሆን ይህም <እርሱን ሚመስል የለም፤እርሱም ሰሚም ተመልካች ነው> የሚለውን የመሰለ አንቀፅን ይገኝበታል።”]
๏ አል-ገዛልይ ፈጣሪውን ጅስም አድርጎ የሳለ አልያ ያሰበ ሰው ከጣኦት አምላኪ ጋር ማመሳሰላቸው ጎልቶ የሚታይ ሐቅ ሲሆን ያን አካልም አቆሞ አልያ አስቀምጦ፣ ጭራቅ አልያ የውበት ሞዴል ቢያደርገውም አንዳች ልዩነት እንደማይፈጥር አስፍረዋል።
¤ ሑጀቱል-ኢስላም ኣል-ሙስተስፋ የተሰኘው ኪታባቸው ላይ በገፅ 332 በተመሳሳይ የሙጀሲም ዕምነት ከሚያከፍሩ የእምነት አይነቶች የሚመደብ መሆኑን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
*وقال الغزالي في المستصفى ”أما إذا كفر ببدعته، فعند ذلك لا يعتبر خلافه، وإن كان يصلي إلى القبلة ويعتقد نفسه مسلماً.لأن الأمة ليست عبارة عن المصلين إلى القبلة، بل عن المؤمنين، وهو كافر، وإن كان لا يدري أنه كافر“
② [«በቢድዓው የከፈረ እንደሆነ በዛ ግዜ ልዩነቱ ቦታ አይሰጠውም።ወደ ቂብላ ዞሮ በመስገድ እራሱን ሙስሊም አድርጎ ቢያስብም፤ ምክነያቱም ኡማህ ሲባል ወደ ቂብላ ዞረው የሚሰግዱ ሰዎች ገለፃ ሳትሆን ይልቅንስ የትክክለኛ አማኞች ናት።ይህ ደግሞ ካ*ፊር ነው።መክፈሩን ባያውቅም»]።
¤ በተመሳሳይ መልኩ ከመሞታቸው ከሶስት ቀን በፊት በፃፉበት የመጨረሻ ኪታባቸው ከሚሰኘው ውስጥ አንዱ የሆነው በኢልጃሙል ዓዋም ገፅ 5 ላይ ፍንትዋ አድርገው ሽምያ፣ማሽሟጠጥ ሆነ ማጣመም በማይቀመስበት ቃላት የሙጀሲምን ከሃዲነት በኢጅማዕ መሆኑን ያሰፍራሉ፦
وقال أبو حَامِدٍ الغَزَالِيُّ في كتابِهِ المسمَّى إِلْجَامَ العَوَامِّ عَنْ عِلْمِ الكَلَامِ ما نَصُّهُ: «فَإِنْ خَطَرَ ببالِهِ أَنَّ اللهَ جسمٌ مُرَكَّبٌ مِنْ أعضاءٍ فهو عابدُ صَنَمٍ؛ فَإِنَّ كُلَّ جسمٍ هو مخلوقٌ، وعبادةُ المخلوقِ كفرٌ، وعبادةُ الصنمِ كفرٌ لأَنَّهُ مخلوقٌ، وكان مخلوقًا لأَنَّهُ جسمٌ، فَمَنْ عَبَدَ جسمًا فهو كافرٌ بإجماعِ الأُمَّةِ السَّلَفُ منهم والخَلَفُ».اهـ
③[“በአዕምሮ ላይ አሏህን ከክፍለ አካላት የተገጣጠመ ነው ብሎ ካመነ ይህ ሰው #ጣዎትን አምላኪ ነው። ሁሉም አካሎች ፍጡሮች ናቸው። ፍጡርን መገዛት ደግሞ ኩፍር ነው።ጧኦትን ማምለክ ኩፍር ነው ምክነያቱም ፍጡር ስለሆነ። ፍጡር የሆነውም አካል ስለሆነ ነው።አካልን የተገዛ ደግሞ #በዑለማዎች የጋራ አቋም ከሀዲ ነው”]።
¤ ይህም ብቻ ሳይሆን በሙጀሲምና በፀሀይ አምላኪ መሀል ልዩነት እንደሌለም በኣሊቅቲሷድ ፊል ዒቲቃድ ገፅ 34 ላይ ሲጠቅሱ ይህን ይላሉ፦
فإن القائل بأن الله سبحانه جسم وعابد الوثن والشمس واحد〕
[“አሏህን አካል ነው ብሎ የሚል እንዲሁ ጣኦትና ፀሀይ የሚገዙ ሰዎች #አንድ ናቸው”]
∅ አንተ እውነትን ፈላጊ ሆይ ሐቅን ከመናገር ምኑ ነው ሚያስፈራህ?! ኣቡ ሐሚድ መጨረሻ ከእርሱ ቡሀሏ ሌላን ለመፃፍ ብእራቸውን አላነሱም በተባለበት ኢልጃሙል ዐዋም ኪታብ ላይ ሙጀሲማዎች ካፊር ናቸው። ይህም ኢጅማዕን በመመርኮዝ ነው ሲሉህ በግልፅ ፈንትው አድርገው ገልፀውልሀል።ከዚህ ሁሉ ማስረጃ ቡሀሏ ተጨምሮባቸው ነው የሚለው ቢያደናግርህ እውን ከአሏህ ውጪ ያለን በአሏህ ስያሜ አድርጎ ሚገዛን ሙስሊም አድርጎ ሚያስብ ኢማም አለን? እንዲሁ ኺላፍም ተነቅሏል ለማለት ምን ነክቶህ በምንስ ታውረህ ነው?!
አሏህን በዲናችን ላይ ከሚመጣ አደጋ ሰላምን እንጠይቀዋለን።
ሸይኽ ዓብዱሏህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
سلامةُ الدينِ لا يعادلُها شيءٌ
[የዲን ሰላም መሆን ምትክ የለውም]።
↘ በስተመጨረሻም ወንድማዊ ምክሬ የሚሆነው ኪታብን በማንበብ ብቻ እውቀት አይያዝም። ማንበብን ብቻ ተመርኩዞ እውቀት ለመሰብሰብ ሲደከርት የከረመ ሸይኩ ሸይጧኑ ሆኖ እንጂ አልታየም።ለዚህም ታላቁ የሰለፍ ዓሊም ሰሕኑን አል-ማሊክይ ኪታብን (ከመርካቶ) እየሸመቱ ፈትዋ ሚሰጡ ሰዎችን እንዲህ በማለት ይገስፃሉ፦
5
1June 4, 2026 2.6K 6