East Gojjam Zone Education Departmen: post #657 — TG.ME

Forwarded fromABAbebaw Hailu
ለክልልና ሃገር አቀፍ ፈተና የቅ/ዝግጅት ስራ ውይይት ተካሄደ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ2015 ዓ/ም የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል የክልልና ሃገር አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና ኦረንቴሽን ከአጋር አካላት ጋር ሰኔ 7/2015 ዓ/ም ተካሄደ፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ውይይቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን የምክክሩ ዓላማ በእየጊዜው በአፈታተን ስርዓት ውስጥ የሚስተዋሉ ልዩ ልዩ ግድፈቶችን ለማረቅ እንዲያመች ነው ካሉ በኋላ በተለይም ባለፈው ዓመት የነበረው የፈተና ስርዓት በተማሪዎቻችን ላይ የተስተዋለው የስነ ምግባር እና የሞራል እንከን የዞናችንን ህዝብ ባህልና እሴት የማይመጥን ክስተት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የደብር ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ይኸይስ ሃረጉ ዶ/ር “ጊዜና ተስፋ የተማሪ ትልቁ ሃብት ነው” ጊዜው አሁን በእጁ የያዘው የሚጠቀምበት ማንም የማይነጥቀው፤ ተስፋው ደግሞ ወደፊት አሻግሮ የሚያየው እድል መሆኑን ገልጸው በ2014 የነበረው የፈተና አፈጻጸም በተፈታኞች የነበረው የስነ ልቦና መዋዠቅ ወይም መንዘቃዘቅ እንዲሁም የስነ ምግባር መዛነፍ የእውቀትና የጽንሰሃሳብ አለመዋቀር ይህም የኩረጃ ባህል ጎልቶ መታየቱ፤እንዲሁም በወሬ ወይም አሉባልታ መፈታት ትልቁ የፈተና አስተምሮት የነበረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የ21ኛው ክ/ዘመን የፈቀደውና የፈለገው እንዲሁም የሚጠይቀውን ተግባር ለመፈጸም ከተሰብሳቢው ትልቅ ቁምነገር እንደሚጠበቅ አጽንዖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የዞኑ ትምህርት መምሪያ ም/ሃላፊ አቶ ደመላሽ ታደሰ የ2014 ዓ/ም የፈተና አፈጻጸም የተዘጋጀውን ሰነድ በማቅረብ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የዞናችንን ገጽታ ሊያሻሽል በሚችል መልኩ ለመስራት በስነምግባር፣ስነልቦና እና በሞራል የታጀበ ዜጋ ለመፍጠር መስራት ይገባል በማለት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
👍9❤3
June 14, 2023 6.4K 4