እንዴት አመሻችሁ ወገን?
~~~
በቀሪ ጊዜያት የትምህርት ስራዎቻችንን ውጤት ሊያመጣ በሚያስችል መልኩ ለመምራት ያመች ዘንድ በየሳምንቱ የማይቆራረጥ የሪፖርትና የመረጃ ቅብብሎሽ ማድረግ ግድ ይላል።
በዚህ መሰረት ሁሌም በየሳምንቱ ሀሙስ እስከ 10:30 ብቻ በዋትስአፕ እና በቴሌግራም በተቀመጠው ቢጋር መሠረት መረጃ መስጠት የግድ ይላል።
የሪፖርት ማድረጊያ ቢጋር፤
~~~
1. የትም/ቤቶች መሠረተ ልማት ማሟላት ያለበት ሁኔታ፤
~በህ/ብ ተሳትፎ የሚገነቡ ግንባታዎች፤
~በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚገነቡ ግንባታዎች ፤
~ትም/ቤቶችን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ እየተሠሩ ያሉ ስራውች፤
2. የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማብቃት የተከናወኑ ተግባራት፤
3. የትም/ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተሠራ ስራ
~ትም/ቤቶችን ደረጃ 4 የማድረስ ስራችን
~ደረጃ 1ትም/ቤቶችን በሙሉ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ፤
4. የጎልማሶች ትም/ት አፈፃፀም
~የጎልማሶች መሠረታዊ ትም/ት አሠጣጥ፤
~የብርሃን ምዘና ምዝገባ አፈፃፀም
5. የተማሪ ማቋረጥና ማሳለስ ለመከላከል እየተሠራ ያለ ስራና የተገኘ ውጤት፤
6. የኢንስፔክሽን ስራ ያለበት ሁኔታ፤
7. የጥናትና ምርምር ሲንፖዚየምና የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ኢግዚቪዥን ማካሄድ፤
8. ወረዳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ ፕሮግራም በማስኬድ ንቅናቄ የመፍጠር ስራ ያለበት ሁኔታ የሚሉትንና ሌሎችም ተግባራት ካሉ በመጨመር ሁሌም በየሳምንቱ ሀሙስ እስከ ቀኑ 10:30 ድረስ ብቻ ሪፖርት እንዲደረግ ከአደራ ጋር አሳስባለሁ።
ማሳሰቢያ :-
የመምሪያው ቡድን መሪዎች ከተቀመጠው ተግባር አኳያ በየቡድናችሁ የሚመለከታችሁን ተግባራት ክትትል በማድረግ የተጠናከረ ሳምንታዊ ሪፖርት በቴሌግራም መላክ የማይቋረጥ ተልዕኮ ስለሆነ በቅርበት እና በትኩረት አመራር ስጡበት !!
" በጋራ ጥረታችን ወደ ቀደመ ከፍታችን !!"
36
9May 2, 2023 7.1K 9