East Gojjam Zone Education Departmen: post #648 — TG.ME

የዘጠና ቀናት እቅድ በማስተዋወቅ ሂደት ገቢራዊ ሆነ
የመጪዎቹ ዘጠና ቀናት እቅድ ለትምህርት መምሪያ ሰራተኞች ገለጻ ተደረገ፡፡
አቶ ጌታሁን ፈንቴ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የቀጣይ ሶስት ወራት እቅድ ሲያስተዋውቁ ያለፉትን ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም እርካብ በማድረግ ነው ፤ያለፉት ወራት እቅድ አፈጻጸም ለክልሉ ከፍተኛ ግብዓት ሰጥቷል ያሉት ሃላፊው ለሚቀጥሉት ዘጠና ቀናት ነጸብራቅ ሆኗል በማለት አክለዋል፡፡ ይህንንም በተጋጋለ መንፈስ መቀጠል እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ እቅዱ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አስጨርሶ ማስመረቅ፤የት/ቤት ደረጃ ማሻሻል፤የተማሪ አሳላሽን በቅርበት መከታተል፤የት/ቤቶችን አቅም ማጠናከር እና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በመሳሰሉት አምስት ዋና ዋና የትኩረት አምዶች ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም እያንዳንዳቸው በጣም ሰፊ ጽንሰ ሃሳብ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሁሉንም ተግባራት መፈጸም የሚያጠነጥነው በተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር መሻሻል ላይ ስለሆነ የተማሪዎች አሳላሽና አቋራጭን ለመቀነስ፤ የእለት ውሎን ከ95% በላይ ማድረግ ፤ በዚህ ዓመት የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የተጣለውን ግብ ለማሳካት ስራ መስራት፤ በ9 ወረዳዎች እዲስ እየተገነቡ ያሉ 11 የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በተመደበው 389836477 ብር በጥራትና በፍጥነት ማስጨረስ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በነገራችን ላይ ፕሮጀክቶች በአልማ፣ በክልል ባለሃብቶችና በማችንግ ፈንድ እየተገነቡ ቢሆንም በግንባታው ከፍተኛውን ድርሻ ለያዘው አልማ የተለየ አድናቆት እንዲቸረው ምስል ፈጥረዋል፡፡
April 13, 2023 5.5K 1