እንዴት ናችሁ ወንድም፤እህቶቼ እንዲሁም የስራ አጋሮቼ..!?
~~
እንደሚታወቀው በዚህ አመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በልዩ ሁኔታ ለፈተና በማዘጋጀት የተሻለና ቀዳሚ ውጤት ማስመዝገብ አለብን ብለን ተግባብተን ወደ ስራ ገብተናል።
በዚህ መሰረት በርካታ ወረዳዎችና አስፈታኝ ት/ቤቶች በሚገርም የስራ ተነሳሽነትና የኃላፊነት ስሜት ተግባሩን እየመሩ ይገኛሉ። በዚህም ልዩ የድጋፍ ፕሮግራም ማለትም:-
- በተመረጡ መምህራን፤
- የተመረጡ የትምህርት አይነቶች፤
- ለመምህራን ማበረታቻ በጀት ተመድቦ፤
- የራሱ ፕሮግራም ወጥቶለት፤
- በማታ እና በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም ተማሪዎቻቸውን በተሟሟቀ መንገድ ለፈተና እያዘጋጁ ይገኛሉ።እጅግ እናከብራችኋለን፤ጠንክሩልን እንላለን !!
በተቃራኒው ደግሞ በተለመደው መንገድ የሚጓዙና የተለመደውን ጅምላ የቲቶሪያል በመስጠት ተማሪዎችን እያገዝን ነው በሚል ራሳቸውን፤ህዝባቸውን እንዲሁም ተማሪዎቻቸውን በሚያታልል መንገድ ተግባር የሚፈጽሙ ጥቂት ወረዳዎችና ት/ቤቶች መኖራቸውን ታዝበናል።
ነገርዮሹ ሁሉ "ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥስ" እንዳይሆንብን የተሰጠውን ዞናዊ አቅጣጫና ተልዕኮ ለምን እናንጠባጥባለን? እኩል መፈጸምስ ለምን አቃተን? ሌሎቹ የሰሩትን ስራ እኛ ለምን አልሰራንም? የሚሉ ጥያቄዎችን ለራሳችን በመጠየቅ ጉድለቶችን ፈጥነን ማረም ግድ ይለናል።
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻችንን በአግባቡ አዘጋጅተን የማሳለፍ ያለማሳለፍ ጉዳይ እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ ተራ አጀንዳ ሳይሆን የህዝባችንን ሞራል የማስጠበቅ፤ያለማስጠበቅ እንዲሁም የክብር ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ አንስተን መክረንበታል።
ስለሆነም "ልዩ ድጋፍ ምንድነው?" የሚለውን ነገር በት/ቤቱ ከሚገኙ መምህራንና ሰራተኞች ጋር በአግባቡ መክሮ ተገቢውን አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደስራ መግባት ግድ ይለናል።
ቀጣይ ሳምንት ጀምረንም 12ኛ ክፍል አስፈታኝ የሆኑ ት/ቤቶችን ምልከታ እናደርጋለን።በምልከታችንም ለተማሪዎች እየተደረገ ያለውን የልዩ ድጋፍ ፕሮግራም እንጎበኛለን(በተለይ የማታ እና የቅዳሜና እሁድ ትምህርቱን) አሰጣጥ በአግባቡ እንፈትሻለን።
& የተማሪዎቹን የDRS ምዝገባ በጣም በጥንቃቄ ሰርተን በአጭር ቀን እናጠናቅ!!
ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችንም የሚደረገው ልዩ ድጋፍ በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠናክሮ እየተሰጠ መሆኑን ወረዳዎች ቸክ አድርጉ፤ከተማሪዎች የዕለት ውሎ መቀነስ ጀምሮ መታረም ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ ታዝበናል።
በጥቅሉ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በአይነቱ ልዩ የሆነ የቅድመ-ዝግጅት ስራ ሰርተን አስደማሚ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሌም ሳንዘነጋ እንስራ።አጠቃላይ ሃገራዊና ክልላዊ ውድድሩ በእጅጉ የከረረ ነው፤በውድድር መሸነፍ ደግሞ ምን ያህል አንገት እንደሚያስደፋ እናውቃለን፤አንገታችንን ቀና ለማድረግ ደግሞ ዛሬውኑ የሚሰጠንን አቅጣጫ ተቀብለን ሳናንጠባጥብ እንፈጽም፤ስኬት ማስመዝገብ ደግሞ እንችላለን !!
" በጋራ ጥረታችን ወደ ቀደመ ከፍታችን !!"
10
2April 4, 2023 6.2K 5