EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት): post #582 — TG.ME

የሀዘን መግለጫ !

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች፣ ዓለም አቀፍ ዳኛ እና አመራር የነበሩት አንጋፋው የእግር ኳስ ሰው ጌታቸው ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጌታቸው ገብረማርያም በተጫዋችነት ለኦሜድላ እና ጥጥ ማኅበር እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውተው ያሳለፉ ሲሆን በመቀጠል ለረጅም ዘመናት በዓለም አቀፍ ዳኝነት ጭምር በሚታወቁበት የዳኝነት ሙያ አገልግለዋል። ከዳኝነት ከተገለሉ በኋላም በኮምሽነርነት፣ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች በጥቅሉ ከ60 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በማገልገል አሳልፈዋል።

የአቶ ጌታቸው ገብረማርያም ሥርዓተ ቀብር በነገው ዕለት በአማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 9፡00 ይፈፀማል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በእኚህ ታላቅ የእግር ኳስ ሰው ጌታቸው ገብረማርያም ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ይመኛል።
May 14, 2026 3.3K 2