አርሰናሎች ከትላንቱ የለንደን ደርቢ ጣፋጭ የድል ፅዋ በኃላ ለሁሉም አንድ ነገርን አሳስበዋል!!!
ይህም ምንድነው አሁንም ቢሆን በሊጉ ምርጥ ቡድን እንደሆኑ ነው። አስፈላጊው ነገር ደግም ለምን አሁንም ምርጥ ሆነው እንዳሉ መረዳት መቻል ይመስለኛል። የትላንቱ ጨዋታ ደግሞ ያንን አሳይቶናል።
በትላንቱ ጨዋታ ቼልሲዎች በአሪፉ ነበር የጀመሩት። ሞርጋን ሮጀርስ ገና ከመጀመሩ አስቆጥሯል። ይህ ግብ ደግሞ በትልቅ ጨዋታ ሙሉ በ ሙሉ ሳይኮሎጂን ሊቀየር የሚችል ዓይነት አጀማመር ነው።
ቼልሲዎች ሲያስቆጥሩ ያኔ አርሰናሎች በጨዋታው ላይ ገና መረጋጋት እየጀመሩ ነበር። በሊጉ ያስተናገዱት የመጀመሪያ ግብም እንደሆነ ይታወቃል።
ያ ሲሆን ግን መድፈኞቹ ፓኒክ አላደረጉም ወይም አልተደናገጡም። ያኔ ስለተመሩ ብቻ ጥድፊያ ውስጥ አልገቡም ወይም ደግሞ ስለተመሩ ብቻ በመጥፎ ሁኔታ አልተጫወቱም። ወደ ኖርማል ስታይላቸው ብቻ ነው የተመለሱት።
ቼልሲን ወደ ኃላ ገፍተዋል ፣ ሚድፊልድ ላይ ስፔሶችን ሲያጠቁ ነበር ከዛ ቀስ በ ቀስ ደግሞ ጨዋታውን ተቆጣጥረውት ተገኝተዋል።
ይህ ነው እንግዲ አሁን ያለው አርሰናል እና ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረው አርሰናል ትልቁ ልዩነት። ግብ ሲያስተናግዱ የሚጫወቱበትን መንገድ እንዲቀይሩ አያደርጋቸውም።
ከዛ ባለፈ ግብ ያስቆጠረው ካይ ሀቨዝ ያስመለከተው እንቅስቃሴ በግሌ በጣም ወድጀዋለሁ።
ሀቨዝ ሊንክ ፕሌይ ፣ ፊዚካል ፕረዘንስ ሲሰጣቸው ነበር ከዛ ባለፈም ያደርግ የነበረው እንቅስቃሴ የቼልሲ ተከላካዮችን ምቾት የነሳ ነበር።
ለምሳሌ የማሸነፊያ ግቧን እናንሳ:- ግቡ ስለ አርሰናል ብዙ ነገር ይናገራል። ዞሊስ ኳሱን ዴሊቨር አደረገ ሀቨዝ ኳሱን የሚጫወት አስመስሎ ከዛ ግን በሚገርም ሁኔታ ለቀቀው ከዛ ኦዴጋርድ በትክክለኛው ፖዚሽን ላይ በመገኘት እንግዲ ጨርሶታል!
ይህንን ቅፅበት ስናነሳ ግን ይህ ስለ ሀቨዝ ብቻ አይደለም። ልዩ ስራ የሰራው አንድ ተጫዋች ብቻ ሳይሆን የቡድን ስራ ነበር። በርካታ ተጫዋቾች የማጥቃት ሁኔታውን በተመሳሳይ ሁኔታ እና በተመሳሳይ ሰዓት የተረዱበት አስገራሚ የቡድን ስራ ነበር።
ያ ነው እንግዲ አርሰናል አሁንም ከምርጦች መካከል አንዱ ናቸው ስል ይህንንም የሚገልፅ ነው። ስላልተሸነፉ ብቻ አይደለም ፤ በጣም የተሟሉ ቡድን ስለሆኑ ነው።
በሌላ በኩል ቼልሲዎችም ዘንድሮ የምር ተፎካካሪ ቡድን መሆናቸውን አሳይተዋል።
ፔስ አላቸው ፣ ቴክኒካል ጥራት ፣በካውንተር ሊጎዱህ የሚችሉ ተጫዋቾች እና ብዙ ግላዊ ተሰጥኦ ያሏቸው ተጫዋቾች አሏቸው።
ነገርግን አርሰናሎች ከባድ ሁኔታዎችን በተሻለ ሁኔታ ማስተናገድ እንደሚችሉ አሳይተዋል።
ትልቁ ልዩነትም እሱ ጋር ነው።
የአርሰናልን ቅርፅ ወይም አጨዋወት ስንመለከት በዕድል የመጣ ሳይሆን ሁሉም ነገር የታቀደበት ነው ማለት ይቻላል። ያው ደግሞ ጠንካራ የተከላካይ ክፍል እንደገነቡ መቼስ ግልፅ ነው። ወደ ሜዳ ወደ ላይኛው ክፍል ገፍቶም መከላከል የሚችል ነው ፣ ሲያስፈልግም በጥልቀት መከላከል ይችላል እና እንዴቱም ሲከላከሉ ቅርፃቸውን እንደጠበቁ ነው።
ቼልሲዎች ነገሮችን ሲለውጡ እና ለአቻነት ሲገፉ እንኳን አርሰናሎች ሙሉ በ ሙሉ ቅርፃቸውን አላጡም ነበር። እርግጥ ነው (Suffer) አድርገዋል ወይም ተሰቃይተዋል ግን ያም ቢሆን በጋራ ሆነው ነው።
እና በመጨረሻም እንግዲ ድል አድርጎ ለመውጣት መንገዱን አግኝተዋል። ትልቁ ምስል እዛ ጋር ይሆናል።
✍ በጋዜጠኛ መኩሪያ አሰፋ
ስለ አርሰናል ምን ይላሉ?
"Share" @dynamicsport
@dynamicsport
3
1September 7, 2026 648 1