ለማርገዝ የተመረጠ (በጣም አመቺ) ቀን የቱ ነው? ለማርገዝ በጣም የተመረጡት ቀናት እንቁላል የሚፈስበት ቀን… — ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias — TG.ME

ለማርገዝ የተመረጠ (በጣም አመቺ) ቀን የቱ ነው?

ለማርገዝ በጣም የተመረጡት ቀናት እንቁላል የሚፈስበት ቀን (Ovulation day) እና ከዚያ በፊት ያሉት 5 ቀናት ናቸው። ይህ አጠቃላይ 6 ቀናት የሚፈጀው ጊዜ "የመውለድ መስኮት" (Fertile Window) ተብሎ ይጠራል።

ለምን? የወንድ ዘር (Sperm) በሴት ማህፀን ውስጥ እስከ 5 ቀናት ሊኖር ይችላል፤ የሴት እንቁላል ግን ከተለቀቀች በኋላ መኖር የምትችለው ለ12-24 ሰአታት ብቻ ነው።

ቀኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል? መደበኛ የ28 ቀናት የወር አበባ ዑደት ላላት ሴት፣ እንቁላል የሚፈሰው የወር አበባ ከመጣበት መጀመሪያ ቀን ጀምሮ ሲቆጠር በ14ኛው ቀን አካባቢ ነው።

ስለዚህ ለማርገዝ ምርጡ ጊዜ ከ9ኛው ቀን እስከ 14ኛው ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ግንኙነት ማድረግ ነው።

ለበለጡ መረጃዎች ዌብሳይታችንን ይጎብኙ 🌎
https://healthtipsethio.blogspot.com/
👍4❤1
August 22, 2026 6K 10