በወንድ አካል ላይ ያለው የፕሮስቴት እብጠት (BPH) በወሲብ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የፕሮስቴት ሕክምናዎች… — ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias — TG.ME

በወንድ አካል ላይ ያለው የፕሮስቴት እብጠት (BPH) በወሲብ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ
 
የፕሮስቴት ሕክምናዎች የወንድ ብልት አለመቆም ችግርን (Erectile Dysfunction) ሊያስከትሉ ይችላሉ?

የፕሮስቴት እብጠት (Benign Prostatic Hyperplasia - BPH) ካንሰር ያልሆነ የፕሮስቴት እብጠት ሲሆን ከ50% በላይ በሚሆኑ እድሜያቸው ከ50 በላይ በሆኑ ወንዶች ላይ የሚከሰት ነው።

የፕሮስቴት እብጠት ብቻውን አስጊ ባይሆንም ህክምናዎቹ በወሲብ ጤና ላይ ግን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

አንዳንድ መድሃኒቶች፣ በተለይ 5-አልፋ ሪዳክታዝ እንደፊናስቴሪድ (Finasteride) ያሉ ምርቶች የወሲብ ፍላጎትን መቀነስ እና በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የወንድ ብልት አለመቆም ችግርን ሊያመጡ  ይችላሉ።

እንዲሁም አንዳንድ ቀዶ ህክምናዎች፣ ለምሳሌ የሚታወቀው Transurethral Resection of the Prostate (TURP) በወንድ ዘር መርጨት ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ይህም የወንድ ዘር ወደ ብልት ከመሄድ ይልቅ ወደ ሽንት ማጠራቀሚያ እንዲሄድ ያደርገዋል(Retrograde Ejaculation)።

አዳዲስ መመሪያዎች እነዚህን የጐንዮሽ ጉዳቶች ከሕክምናው በፊት ከታካሚው ጋር መወያየት እና የተሟላ ውሳኔ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያስረዳሉ።

****
በ ዶ/ር እሌኒ ሞላ

መረጃ ምንጭ፣ European Association of Urology (EAU).

አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ
https://linktw.in/tiRGPP
❤8
July 27, 2026 4.3K 2