የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ ==============**********=========== ዲዩ: ነሐሴ 10/2018 አ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ከተማ በሜሪጆይ ኢትዮጵያ አማካኝነት ለሚገነባው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ግንባታ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የድርጅቱ ኃላፊዎች በተገኙበት የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት በኩል የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አንስተው፣ የሜሪጆይ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ተቋሙ የበኩሉን እንደሚወጣ አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው በሆስፒታሉ አማካኝነት ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ መሠል የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግም አንስተዋል። የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)ሜሪጆይ የኩላሊት እጥበት ማዕከል በከተማው መገንባቱ በጤናው ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እንደሚሆን ገልፀው፣ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንዲበቃ ባለድርሻ አካላትን ለማስተባበር እና ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልፀዋል። በከተማው የሜሪጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ማዕከል መገንባ፣ የማህበረሰቡን የጤና ዘርፍ ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ሚላ እንደሚኖረው የገለፁት ደግሞ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የዲላ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ግርማ ደብረ ናቸው። ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር እና ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ማዕከሉ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ በትብብር ለመስራት እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ማዕከሉን እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ በመድረኩ ተገልጿል። #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲው #UniversityOfTheGreenland
የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ ==============**********=========… — Dilla University Official — TG.ME
August 16, 2026 4.9K 3