ታሪካዊ የምስራች ለስፖርት ቤተሰቡ! ** ✨ የዓለማችን ቁጥር አንድ ሊግ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ… — Linklayer Crypto — TG.ME

💐 ታሪካዊ የምስራች ለስፖርት ቤተሰቡ!
**

የዓለማችን ቁጥር አንድ ሊግ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ — አሁን በነፃ ወደ ቤትዎ ሊመጣ ነው!

📿 በኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ታሪክ ግዙፍ የስፖርት ሁነቶችን ለህዝብ በማቅረብ ፈር ቀዳጅ የሆነው ሀገሬ ቴሌቪዥን፣ የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነፃ አየር ስርጭት (FTA) ብቸኛ ባለመብት በመሆን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል!

🕯 ሀገሬ ቴቪ በቀጣዮቹ ሁለት ተከታታይ የውድድር ዘመናት ያለምንም ክፍያ የሚከተሉትን ድንቅ ዝግጅቶች በነፃ ወደ ቤትዎ ያደርሳል፦

🐬 በሳምንት አንድ ጨዋታ፦ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 11፡00 ላይ የሚደረጉ የተመረጡ አጓጊ
     የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያዎች።

🔺 የሰኞ ምሽት ማጠቃለያ (Highlights)፦ የሳምንቱን ሙሉ ጨዋታዎች ግቦችና ምርጥ
      እንቅስቃሴዎች።

🚨 የረቡዕ ምሽት ዘጋቢ ፊልም (Documentary)፦ በፕሪሚየር ሊጉ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ
     ሳቢና ማረኪ ታሪኮች።

🧷 የአርብ ምሽት ቅድመ-ጨዋታ (Preview)፦ ሳምንታዊ የጨዋታዎች ትንተና እና ዝግጅት።

🛡 ሀገሬ ቴቪ ይሄን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስርጭቱን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ተመልካቾች ያለምንም ክፍያ በቤታቸዉ በነፃ ያደርሳል።
  🤩
❤12⚡1🔥1
August 15, 2026 717 1