ትምህርት ሚንስቴር ማስጠንቀቂያ ሰጠ ❗
ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ባስተላለፈው ይፋዊ መመሪያ ከሚኒስቴሩ ዕውቅና ውጭ በሕገ-ወጥ መንገድ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን የሚያዛውሩና የሚቀበሉ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ላይ ጥብቅ ሕጋዊ ተጠያቂነት እንደሚከተል አስጠነቀቀ ።
የሪሚድያል ተማሪዎች በዝውውር ወደመረጡት ዩንቨርስቲ ይቀይሩ እንደነበር dbu daily news ያነጋገራቸው ተማሪዎች የተናገሩ ሲሆን ይህ ተግባር ሊቀጥል እንደማይችል ከተላከው ደብዳቤ ለመረዳት ችለናል።
ሚኒስቴሩ አደረኩት ባለው ጥናት ተማሪዎች ከተመደቡበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውጭ የአሠራር ፍትሐዊነትን በሚጥስ መልኩ ዝውውር እያደረጉ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ከዚህ በኋላ ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ ተማሪዎችን ማዛወርም ሆነ ተቀብሎ ማስተማር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል ።
ይህንን መመሪያ ጥሶ በሚገኝ
በማንኛውም ተቋም እና አመራር ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ሚኒስቴሩ በደብዳቤው ላይ በግልጽ አስገንዝቧል ።
ለፈጣን እና ታማኝ የመረጃ ምንጭ dbu daily news ን ተቀላቀሉ።
@dbu11
@dbu111

7
2August 28, 2026 3.9K 8 5