የአለማችን ትንሹ ፕሮፌሰር የ18 ዓመቱ ድንቅ ታዳጊ❗ ሰላም ለእናተ ይሁን የ dbu daily news ቤተሰቦች… — DBU Daily News — TG.ME

የአለማችን ትንሹ ፕሮፌሰር የ18 ዓመቱ ድንቅ ታዳጊ
ሰላም ለእናተ ይሁን የ dbu daily news ቤተሰቦች በጊነስ ወርልድ ሪከርድ ያገኘነውን መረጃ እናካፍላችሁ።

​በአብዛኛው የልጅነት ጊዜ በጨዋታና በትምህርት ልምምድ የሚያልፍ ቢሆንም፣ የ18 ዓመቱ አሜሪካዊ ናታን ቶማስ ግን በልዩ ተሰጥኦው ዓለምን ማስደመሙን ቀጥሏል።

​በቅርቡ ይፋ በሆነው የጊነስ ወርልድ ሪከርድ መረጃ መሠረት፣ ናታን በታሪክ የዓለማችን ትንሹ ፕሮፌሰር እና የዩንቨርስቲ መምህር በመሆን በይፋ ተመዝግቧል። ይህም በ1717 በ19 ዓመቱ አሰልጣኝ በመሆን በስኮትላንዳዊው የሂሳብ ሊቅ ኮሊን ማክላውሪን ተይዞ የነበረውን የብዙ ዘመናት ክብረ ወሰን መስበር ችሏል።

​ገና በሕፃንነቱ መራመድና መናገር ሲጀምር የነበረው የሂሳብና የሳይንስ ተሰጥኦ፣ እኩዮቹ ካርቱን በሚመለከቱበት ዕድሜ ውስብስብ የፊዚክስ ቀመሮችን ወደ መፍታት አሸጋግሮታል። በአሁኑ ወቅትም ከእርሱ በ3 እና በ4 እጥፍ ዕድሜ የሚበልጧቸውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በብቃት እያስተማረ ይገኛል።

​"አንዴ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኋላ ዋናው ነገር እውቀት ነው ዕድሜ ለውጥ አያመጣም" የሚለው ናታን በ10 ዓመቱ ኮሌጅ ገብቶ በ14 ዓመቱ ወደ ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ ተዛውሮ በ18 ዓመቱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪውን በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ አጠናቆ ማስተማር የጀመረና በማያሚ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኝ ድንቅ ታዳጊ ለጊነስ ወርልድ ሪከርድ በሰጠው ቃለ መጠይቅ እቅዱ ኢንጂነሪንግን ከሕግ ጋር በማጣመር በአእምሯዊ ንብረትና ፓተንት ዘርፍ ትልቅ አሻራ ማሳረፍ እንደሆነ ተናግሯል።

@dbu11
@dbu111
👌8🤬1
August 9, 2026 9.2K 6