የዲጂታል ቀማኞች ወጥመድ እና የአንድ ቤተሰብ የዕድሜ ልክ ጥረት መክሸፍ❗
"ቤት ቁጭ ብለው በወር እስከ 100 ሺህ ብር ያትርፉ" በሚል ማራኪ የማኅበራዊ ሚዲ ያ ማስታወቂያ የተጠመደው የኦንላይን ማጭበርበር፣ በአንድ የፌደራል ፖሊስ አመራር ቤተሰብ ላይ ከባድ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትሏል።
በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ያገለገሉት ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት ሽመልስ ባለቤት፣ "አሊባባ ኦንላይን ንግድ" በተሰኘ የሀሰት የቴሌግራም እና ዋትስአፕ መዋቅር ውስጥ በመግባት ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ተዘርፈዋል። አጭበርባሪዎቹ መጀመሪያ ላይ ለይስሙላ የ800 ብር ክፍያ የ1,500 ብር ትርፍ በመመለስ እምነት ካተረፉ በኋላ፣ ሰለባዋ የራሳቸውን የቁጠባ ገንዘብና ከውጭ ሀገር እህታቸው የተበደሩትን 600 ሺህ ብር ጨምረው እንዲያስገቡ በማድረግና በሐሰተኛው መተግበሪያ ላይ የ3 ሚሊዮን ብር ትርፍ እንዳላቸው በማሳየት፣ "ከፍተኛ ግብር መክፈል አለባችሁ" በሚል ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስገቡ ያደርጋሉ በመጨረሻም ገንዘቡን ማውጣት ሳይችሉ ቀርተው አካውንታቸው ላይ 59 ብር ብቻ የቀረ ሲሆን፣ ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት በስራ ስምሪት ላይ እያሉ ሙሉ የዕድሜ ልክ ጥረታቸው ተበልቷል።
ይህን የገንዘብ መዘረፍ ያወቀችው ባለቤታቸው በድንጋጤ በመታመማቸው፣ በአሁኑ ወቅት በጸበል ቦታ ይገኛሉ። ይህ በሰይፉ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ጭምር የቀረበው መረጃ፣ የዲጂታል ማጭበርበሮች እያደረሱ ያሉትን ጥፋት የሚያሳይና ህዝቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚያስገነዝብ ነው።
እኛም የdaily news ቤተሰቦች ይማሩበታል ብለን መረጃውን ስናጋሪችሁ የመረጃ ምንጫችንን ገርሻ page የተሰኘን የፌስቡክ ገፅ አድርገን ነው።
ልብ ልትሉት የሚገባ ነገር ምንም ነገር በነፃ የለም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ና መሰል ነገር የሚገኘው ከእርዳታ ድርጅቶች ብቻ ነው እሱም በቅድመ ሁኔታዎች ። እንደዚህ አይነት አጓጊ ሁኔታዎች ሲገጥሙን መጠርጠር እና እነሱ የሚያገኙት ጥቅም ምንድነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል።
@dbu11
@dbu111
7
4August 9, 2026 9.6K 16