የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አስታውቋል። በክልሉ ከተፈተኑት 173,699 ተማሪዎች መካከል 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡት 135,003 (77.72%) ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን
ከከፍተኛ ውጤት አስመዝጋቢዎች ዳዊት አማረ አለማየሁ ከሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ ኩርባ ትምህርት ቤት በፈተናው የተሰጡትን ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ በመመለስ Average 100 በማምጣት ቀዳሚ መሆን ችሏል።
ውጤት ለመመልከት እና ቅሬታ ለማቅረብ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይቻላል፦
በድረ-ገጽ ለማየት፦ amhara.ministry.et/result ላይ በመግባት፣ የተማሪውን መለያ ቁጥር (ID) እና ስም በአማርኛ አስገብተው 'Check your result' የሚለውን ይጫኑ።
በቴሌግራም ቦት ለማየት፦ @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ በመግባት 'Start' የሚለውን ይጫኑ፤ በመቀጠል ክፍልዎን እና ክልልዎን መርጠው የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምዎን በማስገባት ማየት ይችላሉ።
ቅሬታ ለማቅረብ፦ በውጤቱ ላይ ቅሬታ ካለዎት በዚህ ሊንክ ማቅረብ ይችላሉ፦ amhara.ministry.et/complaint
ማሳሰቢያ፦ ድረ-ገጾቹን ከመጠቀምዎ በፊት ቪፒኤን (VPN) አብርተው ከሆነ ማጥፋት ይኖርብዎታል።
በተያያዘ ዜና የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚሆን ቢሮው ገልጿል።
August 2, 2026 7.1K 15