ኢትዮጵያ በዓመት ከ150,000 እስከ 300,000 ሜትር ኪዩብ የኤም.ዲ.ኤፍ (MDF) ምርት ፍላጎት እንዳላት… — Development Bank of Ethiopia (DBE) — TG.ME

ኢትዮጵያ በዓመት ከ150,000 እስከ 300,000 ሜትር ኪዩብ የኤም.ዲ.ኤፍ (MDF) ምርት ፍላጎት እንዳላት ይገመታል። በዘርፉ አምራቾች ቢኖሩም፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎት ባለመሸፈኑ ምርቱ አሁንም በስፋት ከውጭ ሀገር ይገባል።

ይህንን የገበያ ክፍተት የሚቀይር ግዙፍ ፋብሪካ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ማጠናቀቂያው ላይ ይገኛል። ስቲሊ ዲቢ ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘው ይህ ፋብሪካ ያለቀለት (Finished) የኤም.ዲ.ኤፍ ምርት በስፋት የሚያመርት ይሆናል።

የፋብሪካው ዋነኛ አበርክቶዎች፡

oየሀገር ውስጥ ፍላጎትን መሸፈን፡ ፋብሪካው የ18 ሚሊሜትር ውፍረት ያለውን ኤም.ዲ.ኤፍ ብቻ በዓመት 91,500 ሜትር ኪዩብ ያመርታል።

oከፍተኛ የማምረት አቅም፡ በተጨማሪም የ17 ሚሊ ሜትር ውፍረት ያለው የኤም.ዲ.ኤፍ ሰሌዳ በቀን እስከ 70,000 ያመርታል።

oየሀገሪቱን የኤም.ዲ.ኤፍ ፍላጎት እስከ 70% መሸፈን ያስችለዋል።

oየጥሬ ዕቃ አጠቃቀም፡ የባህር ዛፍ ተክልን በዋና ጥሬ ዕቃነት በመጠቀም የአካባቢውን የደን ሀብት ጥቅም ላይ ያውላል።

oኢኮኖሚያዊ ጥቅም፡ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በማርካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከማዳኑ ባሻገር፣ ምርቱን ለጎረቤት ሀገራት ገበያ የማቅረብ አቅም አለው።

oየሥራ ዕድል፡ ፋብሪካው ለ1,500 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፋይናንስ የተገነባው የዚህ ግዙፍ ፋብሪካ ግንባታ፣ በባንኩ ጥብቅ የፕሮጀክት ክትትልና ግምገማ ታግዞ በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ ተጠናቋል።

የማሽን ተከላ ሥራው አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ለመግባት የጥቂት ወራት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል።

#DBE #mdf
👍4❤3
September 3, 2026 1.4K