የአፍሪካ ልማት ባንክ በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን የሚደገፍ የዲጂታል ፋይናንስ ፕሮግራም ይፋ አደረገ።
ባንኩ ከአክሲያን ግሩፕ ጋር በመተባበር ነው ፕሮግራሙን ይፋ ያደረገው።
በአምስት የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ከ34,000 በላይ ነጋዴ ሴቶች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ፕሮግራሙ የዲጂታል ብድር፣ የፋይናንስ ትምህርት ስልጠና፣ የንግድ ማሳደጊያ ስልቶች እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦትን ማሳደግ የሚያስችል አቅም ይፈጥራል።
አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው የሴቶች ሥራ ፈጣሪነት መጠን ያላት ቢሆንም፣ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች 49 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የፋይናንስ ክፍተት ያጋጥማቸዋል። መርሃ ግብሩ ይህንን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና አክሲያን ግሩፕ ይፋ ያደረጉት የዲጂታል ፋይናንስ ፕሮግራም በታንዛኒያ፣ በሴኔጋል፣ በቶጎ፣ በኮሞሮስ እና በማዳጋስካር በሁለት ዙር ተፈጻሚ ይሆናል።
መረጃው የአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡
#DBE #interpreneur

3
1September 3, 2026 1.6K 1