Development Bank of Ethiopia (DBE): post #3095 — TG.ME

የአፍሪካ ሀገራት የሰርኩላር ኢኮኖሚ አቀራረብ (ዘላቂ የምርት እና አጠቃቀም ስርዓት) ፍኖተ ካርታ እያሻሻሉ ነው፡፡

ሰርኩላር ኢኮኖሚ ስርዓት ማለት የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ለማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፎች ወደ ኢንቨስትመንት እድል ለመቀየር የሚያስችል አሰራርን በፖሊሲ ውስጥ ማካተት ነው፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚደገፈው ይህን አሰራር አንጎላ፣ ላይቤሪያ፣ ማዳጋስካር እና ሴኔጋል በሁለተኛው ምዕራፍ ተቀላቅለዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ቤኒን፣ ቻድ እና ሞሪሸስ የሰርኩላር ኢኮኖሚ አቀራረብን በመጀመሪያው ምዕራፍ ውጤታማ ትግበራ ላይ ናቸው፡፡

ሀገራቱ በተለይም በኮንስትራክሽን፣ በደን ልማት፣ በግብርና፣ በፕላስቲክ እና ጨርቃጨርቅ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኢነርጂ እና የውሃ አስተዳደር ዘርፎች ነው ውጤታማ ትግበራ ያደረጉት፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ከሆነ አፍሪካ በየዓመቱ ከ400 ቢሊዮን ዶላር በላይ የልማት ፋይናንስ ክፍተት ይገጥማታል፡፡

ይህን ክፍተት በሰርኩላር ኢኮኖሚ አቀራረብ ሀብት እና ምርታማነትን በሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ በማስቀረት የመዋቅር እሴት ኪሳራን በቀጥታ መቅረፍ እንደሚቻል ባን ያምናል፡፡

ስርዓቱ ምርት ላይ እሴት መጨመር፣ የኢንዱስትሪ እድገትን ማሳደግ እና የሀገር ውስጥ የሥራ እድል ፈጠራን ያስፋፋል፡፡

የሰርኩላር ኢኮኖሚ አቀራረብ ትግበራን ለማስቀጥል ምቹ የፖሊሲ እና የተቋማት አካባቢን ለመፍጠር የሚያስፈልገውን የገንዘብ እና ቴክኒክ ድጋፍ የአፍሪካ ልማት ባንክ እያቀረበ ነው፡፡
መረጃው የአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡
#DBE #Africadevelopmentbank #circulareconomy
👍1
August 24, 2026 2.6K