Development Bank of Ethiopia (DBE): post #3066 — TG.ME

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ያልተማከለ ኤሌክትሪክና መብራት አቅርቦት (ADELE) ፕሮጀክት አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በፕሮጀክቱ የተገኙ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን የተመለከተ ነው፡፡

በተለይም የፋይናንስ ሀብት አጠቃቀምን ማፋጠን፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን ማሳደግ እና የታዳሽ ኃይል መፍትሔዎችን በገጠር ለማስፋፋት የሚያስችሉ ስልቶች ላይ በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም፣ በፕሮጀክቱ ማዕቀፍ የተፈቀደው የተሻሻለ የፋይናንስ አቅርቦት ሞዴል፣ የልማት ባንክ በቀጥታ ለግሉ ዘርፍ የሚያቀርበው የብድር መስኮት፣ እንዲሁም የተሳታፊ የፋይናንስ ተቋማትን ተሳትፎና አፈጻጸም ለማጠናከር የሚደረጉ ሥራዎች በዝርዝር ተገምግመዋል፡፡

የተቋማቱ የልማት አጋርነት በፕሮጀክት አፈጻጸም፣ በታዳሽ ኃይል ተደራሽነት እና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ላይ ውጤታማ ሥራ መከናወኑ ተነስቷል፡፡

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ውይይት፣ የዓለም ባንክ ልዑክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ የኃይል ዘርፍ ፕራክቲስ ማናጀር ሚስተር ሲሞን ጄ. ስቶልፕ ተገኝተዋል፡፡
#DBE #Worldbank #renewableenergy
❤6👍3
August 21, 2026 2K 1