አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል ስምንት 【የመጨረሻው ክፍል 】 ዓኢሻና የአላህ ፍራቻዋ መልዕክተኛው ( ሰለላሁ… — DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] — TG.ME

አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል ስምንት 【የመጨረሻው ክፍል 】 ዓኢሻና የአላህ ፍራቻዋ መልዕክተኛው ( ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ለተወዳጇ ሚስታቸው የነበራቸውን ፍቅር የማያውቅ ማን አለ ? ከማንም በላይ ማንን እንደሚወዱ ሲጠየቁ ዓኢሻን ብለው መልስ ሰጥተዋል ። በኢስላማዊ ህግጋት ከፍተኛ ዕውቀት የነበራት ከመሆኑ የተነሳ ታላላቅ ሶሃባዎች በዚህ ዘርፍ መፍትሄ ፍለጋ ወደ እሷ ይሄዱ ነበር ። ጅብሪል ‹ አስሰላሙ ዐለይኩም › በማለት ሰላምታ ያቀርብላት ነበር ። መልዕክተኛውም በአንድ ወቅት በጀነትም ባለቤታቸው እንደምትሆን ነግረዋታል ። በመናፍቃን ስትታማ አላህ ከሀሜቱ ነፃ መሆኗን ያረጋገጠላት የቁርኣን አንቀጽ በማውረድ ነበር ። ኢብን ሰዕድ እንደጠቀሰው ዓኢሻ ( ረ.ዐ ) በአንድ ወቅት አላህ ከሌሎች የመልዕክተኛው ሚስቶች በተለየ የሰጣትን አሥር ያህል ጥሩ ባህሪዋን ቆጥለች ። እነዚህ ባህሪዎች ቢኖሯትም አላህን ከመፍራቷ የተነሳ የሚከተሉትን ስትል ትደመጥ ነበር ። « ሁል ጊዜ አላህን በማወደስ እንድጠመድና በፍርዱ ቀንም ነፃ እንድወጣ ዛፍ አድርጐ ፈጥሮኝ በነበር ! » « ድንጋይ ወይንም አፈር ባደረገኝ ! » « ቅጠል ወይንም ሳር ባደረገኝ ! » « ባልተፈጠርኩ ! » ከታላቋ ኸዲጃና ከፋጢመቱ ዘህራእ ( አንፀባራቂዋ ) ( ረ.ዐ ) ቀጥሎ ዓኢሻ በኢስላም ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣት ድንቅ ሴት ናት ። በነበራት ጠንካራ ሰብዕና በሁሉም መስክ ማለትም በዕውቀት ፣ በማኅበራዊ ኑሮ ፣ በፖለቲካና በጦር ሜዳ የመሪነት ስፍራ ይዛ ነበር ። ዓኢሻ በዘመኗ ከነበሩ ሴቶች የክብርትነትን ደረጃ ለማግኘትና መልካም አርአያ ለመሆን በቅታለች ። በ 58 ኛው ዘመን ሂጅራም በወርሀ ረመዷን ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተች ። በኑዛዜዋ መሠረት በመዲና በቂዕ በተሰኘው የቀብር ስፍራ ከሌሎች የነቢዩ አስሀባዎች ጋር አስከሬኗ አረፈ ።     ✍ ሙሐመድ ኢብን ፈድሉ         【 📚ሃያቱ ሶሃባ 】         t.me/Darutewhide/2927

👍7
August 10, 2026 1.6K 4