አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል ሰባት የዓኢሻ በአላህ መንገድ ላይ ንብረቷን መቸር አዒሻ ይህን ዓይነቱን ስጦታ ከአሚር ሙዓዊያ ፣ ከአብዱላህ ኢብን ዙበይርና ከሌሎችም በተደጋሚ ታገኝ ነበር ። ምክኒያቱም ያ ጊዜ ብዙ ግዛቶች በሙስሊሞች ቁጥጥር ሥር የወደቁበት ወቅት ስለነበር የድሎት ወቅት ነበር ። የተትረፈረፈ ሃብት ቢኖርም አዒሻ ግን የምትኖረው በዝቅተኛ የአኗኗር ደረጃ ነበር ። ልብ በሉ ! 100 ሺህ ዲርሃም ለድሀ አከፋፍላ ለራሷ ግን ለማፍጠሪያዋ ሥጋ መግዣ ረሳች ። ባሁኑ ጊዜ እንደዚህ ዓይነቱ ክስተት የማይታሰብ ይመስላል ። ነገር ግን በሶሃባዎች ጭንቅላት ይህን ዓይነት በመቶ የሚቆጠር ክስተት ተአማኒነት ነበረው ። በዓኢሻ ( ረ.ዐ ) በርካታ መስሰል ክስተቶች ተነግረዋል ። በአንድ ወቅት ጾመኛ ነበረች ። ለማፍጠሪያዋም ያለ ቁራጭ ዳቦ ምንም ነገር የላትም።ለማኝ መጥቶ ሲለምናት ለአገልጋይዋ ዳቦውን እንድትሰጠው ነገረቻት ። አገልጋይዋም ‹ ዳቦውን ብሰጠው ለማፍጠሪያሽ የሚቀር ነገር የለም ። › ስትላት ዓኢሻም « ምንም አይደለም ስጪው » አለቻት ። በአንድ ወቅት ደግሞ በህልሟ እባብ ገደለች ። የሚከተለውንም ታያለች « ዓኢሻ ሙስሊም ገደልሽ » ይላታል ። እሷም « ሙስሊም ወደ መልዕክተኛው ( ሶ.ዐ.ወ ) ሚስት ቤት መች መጣ ? » ትለዋለች ። በህልሟም ያገኘችው መልስ « የለም ! እባብ ተመስሎ ነው የመጣው » የሚል ነበር ። በዚህን ጊዜ በፍጥነት ከእንቅልፏ ትነሳና በስህተት ከተገደለ ሙስሊም የሚሰጠውን የደም ካሳ –12 ሺህ ዲርሃም– በሰደቃ መልክ በፍጥነት አከፋፈለች ። ኡርዋ ስለ አዒሻ ቸርነት ሲናገር : - « በአንድ ወቅት አዒሻ ( ረ.ዐ ) የራሷ ልብስ የተጣፈ ሆኖ እያለ 70 ሺህ ዲርሃም ስታከፋፍል አይቻታለሁ ። » ብሏል ። የዓኢሻ በኢብን ዙበይር መናደድ ለአብደላህ ኢብን ዙበይር ዓኢሻ አክስቱ ነች ። እሷ ያሳደገችው በመሆኑ በጣም ትወደው ነበር ። ራሷ በችግርና በድህነት እያለች ይህን ያህል በበጐ አድራጐት ላይ ንብረቷን ማዋሏ ደስ አይለውም ነበር ። ይህንን ለአንድ ሰው አንስቶ « አክስቴን ከዚህ አድራጐቷ ማስቆም አለብኝ ። » ብሎ ተናገረ ። ይህ ወሬ ደረሳትና ከመናደዷ የተነሳ አብዱላህን ዕድሜ ልኳን ላለማናገር ማለች ። አብዱላህ ኢብን ዙበይር በመሃላዋ በጣም ደነገጠ ። ብዙ ሰዎችን እንዲያነጋግሩለት ላከ ። የምትሰጣቸው መልስ « ምያለሁ መሃላዬን ለማፍረስ ዝግጁ አይደለሁም ። » የሚል ነበር ። በመጨረሻ ከመልዕክተኛው እናት ዘመዶች ሁለት ሰዎች በአማላጅነት ይዞ ወደ ቤቷ ሄደ ። ዓኢሻ ሰዎቹን ቤት እንዲገቡና ከመጋረጃ ጀርባ እንዲያነጋግሯት ፈቀደች ። ኢብን ዙበይርም ተደብቆ ከሰዎቹ ጋር ገባ ። ሰዎቹ ንግግር ሲጀምሩ እሱ ስላላስቻለው መጋረጃውን አቋ ርጦ ሄዶ እያለቀሰና ይቅርታን እየተማፀነ ተጠመጠመባት ። ሰዎቹም ጣልቃ በመግባት መልዕክተኛው አንድ ሙስሊምን ሌላ ሙስሊም ማኩረፍ እንደከለ ከሉ አስታወሷት ። ሐዲሱን ስትሰማ አላህ እንዳይቆጣባት በመጨነቅ አምርራ ማልቀስ ጀመረች ። ዙበይርንም ይቅር ብላው ማነጋገር ጀመረች ። ከዚያም መሃላዋን ስላፈረሰች ካሳ ይሆን ዘንድ አርባ ባሪያዎችን በተለያየ ጊዜ ነፃ አውጥታለች ። ✍ ሙሐመድ ኢብን ፈድሉ 【 📚ሃያቱ ሶሃባ 】 “ ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ” ¤ t.me/Darutewhide/2852
አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል ሰባት የዓኢሻ በአላህ መንገድ ላይ ንብረቷን መቸር አዒሻ ይህን ዓይነቱን ስጦታ… — DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] — TG.ME
August 7, 2026 1.6K 6