አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል አራት በአንድ ወቅት አዒሻ በወቀሳ መልክ ነቢዩ ለምን አዘውትረው « አንድ… — DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] — TG.ME

አዒሻ ቢንት አቡበክር ክፍል አራት በአንድ ወቅት አዒሻ በወቀሳ መልክ ነቢዩ ለምን አዘውትረው « አንድ የቁረይሽን ባልቴት » እንደሚያነሱ ብጠይቃቸው ልባቸው በሐዘን በመነካት እንዲህ ሲሉ መለሱልኝ : - « እርሷኮ ( ኸዲጃ ) ሌሎች ችላ ሲሉኝ ያመነችብኝ ፣ ውሸታም ሲያደርጉኝ ሐቀኛነቴን ያረጋገጠችልኝ ፣ ሲያገልሉኝ የሐዘኔን ሸክም ለማውረድ ሐብቷን ሁሉ ወጪ ያደረገችልኝ ውድ ባለቤቴ ነበረች ። » አዒሻ ይህ ቅናቷ ለክፉ የማይሰጥ ከመሆኑም ባሻገር ለጋስነቷና ታጋሽነቷ ይህ ነው አይባልም ። ለረጅም ጊዜ የሚቆየውን የነቢዩን የችግርና የረሀብ ጐጆ በትዕግስት ትይዘው ነበር ። ለቀናት የምግብ ማብሰያ እሳት ሳይቀጣጠል ይቆያል ።በዚህን ጊዜም ቤተሰቡ ቴምርና ውኃ በመመገብ ህይወቱን ያቆያል።ታዲያ ዓኢሻ ይህ ሕይወት አላስከፋትም ፤ ጠቀም ያለ ገንዘብ ፃዕዱን የሕይወ ቷን ስልት የማይበግረው ፥ እጅግ የተደነቀች ባለሟል ሴት ነበረች ። በአንድ ወቅት ነቢዩን ሚስቶቻቸው የሌላቸውን ገንዘብ እንዲሰጧቸው ስለወተወቷቸው ከሁሉም ተለይተው ለወር ያህል ቆዩ ። ይህ የሆነው ለስጦታ የሚበቃ እጅግ የተትረፈረፈ ሐብት የተገኘበት የኸይበር ጦርነት ከተደረገ በኋላ ነበር ። ነቢዩ ከወር ሽሽታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሄዱት ወደ ዓኢሻ ቤት ነበር ። እርሷም እርሳቸውን በማየቷ እጅግ ስትደሰት ሁለት አማራጮችን የሚያቀርብላት ወህይ ( ራዕይ ) እንደመጣላቸው ይገልፁላታል ። አባቷን ሳታማክርም ለውሳኔ እንዳትቸኩል በማሳሰብም የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡላት : - يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ إِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا فَتَعَالَيْنَ أُمَتِّعْكُنَّ وَأُسَرِّحْكُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا                         አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው «ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ፤ አጣቅማችኋለሁና፡፡ መልካምንም ማሰማራት (በመፍታት) አሰማራችኋለሁና፡፡【አል-አሕዛብ  28】       ለቀረበላት ጥያቄ ዓኢሻ ማንንም አላማከረችም።የሰጠችው ምላሽ « በእርግጥም እኔ የምሻው አላህንና መልዕክተኛውን ፣ እንዲሁም ዘውታሪ የሆነውን የመጭውን ሕይወት መኖሪያ ( ጀነት ) ነው » የሚል ነበር ። የተቀሩት የነቢዩ ባልተቤቶችም እንደዚሁ የርሷን መሰል ምላሽ መስጠታቸው ይታወቃል ። ✍ ሙሐመድ ኢብን ፈድሉ     【 📚ሃያቱ ሶሃባ 】       “ ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ”       ¤ t.me/Darutewhide/2852

👍12
July 30, 2026 1.5K 3 7