ክልከላ እና ገደብ የተደረገባቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች ዝርዝር 🔑 ክልከላ እና ገደብ የተደረገባቸው የቴክኖሎጂ… — Ethiopian Customs Clearing Agents — TG.ME

⚜ክልከላ እና ገደብ የተደረገባቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች ዝርዝር 🔑 ክልከላ እና ገደብ የተደረገባቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች የትኞቹ ናቸው? 🏵በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1310/2016 መሠረት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች በሀገራዊ ደህንነት ላይ ከሚያደርሱት ስጋት አንፃር በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ተለይተዋል፡- 1⃣ ክልከላ የተደረገባቸው ምርቶች፡- እነዚህ ምርቶች በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደ ሀገር እንዳይገቡ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው። 2⃣ ገደብ የተደረገባቸው ምርቶች፡- እነዚህ ደግሞ ወደ ሀገር ሊገቡ፣ ሊወጡ ወይም ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲሰጣቸው ብቻ ነው። ⚠ ማንኛውም አስመጪ፣ ላኪ ወይም ተጠቃሚ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ከማስገባቱ ወይም ከማስወጣቱ በፊት ምርቶቹ በየትኛው ምድብ ውስጥ እንደሚወድቁ የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። #ኢመደአ #INSA

❤10🙏7👍4😘2
July 15, 2026 7.7K 67