በተመረጡ የገቢ ዕቃዎች ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አመላካች ዋጋዎችን አጠቃቀም በተመለከተ ከብሔራዊ ባንክ… — Ethiopian Customs Clearing Agents — TG.ME

⚜በተመረጡ የገቢ ዕቃዎች ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አመላካች ዋጋዎችን አጠቃቀም በተመለከተ ከብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ማብራሪያ 🔑 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀደም ሲል ማለትም ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም (January 26, 2026) ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሚወጡ አመላካች ዋጋዎች ዓላማቸው የውጭ ምንዛሪ ሂደትን በሚመለከት በገቢ ዕቃዎች ዋጋ ትመና ላይ ወጥነትንና ግልጽነትን ለመደገፍ እንደ ማጣቀሻ ብቻ እንዲያገለግሉ ነው፡፡ እነዚህ አመላካች ዋጋዎች የግዴታ ወይም ቋሚ የመተኪያ ዋጋዎች አይደሉም፡፡ እንዲሁም የአንድን የተወሰነ ግብይት ትክክለኛ ዋጋ ለመወሰን በቀጥታ እንደ አንድ ለአንድ ንፅፅር ሊወሰዱ አይገባም፡፡ 🎯ሰሞኑን የታየውን ብዥታ ለመቅረፍ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች የሚከተሉትን ግልጽ መመሪያዎች አስተላልፏል፦ 🏵ባንኮች በደንበኞች የሚቀርቡ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ ምን ያህል ተገቢ መሆኑን ለመገምገም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን አመላካች ዋጋዎች እንደ ማጣቀሻ መረጃ መጠቀም አለባቸው፡፡ 🏵ባንኮች የዋጋ ንጽጽር እንዲያደርጉ የታዘዙት በአመላካች ዋጋዎችና በደንበኞች በሚቀርቡ ዋጋዎች መካከል የተጋነነ ወይም ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን ሲያስተውሉ ብቻ መሆኑን በዛሬው እለት ጥር 30 ቀን 2018 ማብራሪያ ሠጥቷል::

❤12👍4👏1🙏1
February 7, 2026 11.3K 45