የገንዘብ ሚኒስቴር በወቅቱ ያልተሰበሰበ የማህበራዊ ልማት ቀረጥን በተመለከተ ህዳር 23/2018 በቁጥር… — Ethiopian Customs Clearing Agents — TG.ME

የገንዘብ ሚኒስቴር በወቅቱ ያልተሰበሰበ የማህበራዊ ልማት ቀረጥን በተመለከተ ህዳር 23/2018 በቁጥር ታፖመ/ነ/364/18 ለጉምሩክ ኮሚሽን በተጻፈ ደብዳቤ ጉዳዩ ውሳኔ ሳያገኝ ተንጠልጥሎ መቆየቱ በኮሚሽኑ እና በግብር ከፋዮች መካከል የታክስ አስተዳደር ችግር እየሆነ በመምጣቱ ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ በማየት የታክስ ዕዳ ማቃለያ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት÷ በዚሁ መሠረት 🔑 ፍሬ ግብሩ መከፈሉ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ 1. በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 648/2001 (እንደተሻሻለ) አንቀፅ 13(3) ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በፍሬ ግብሩ ላይ የተጠየቀው ወለድ ቀሪ እንዲሆን፣ 2. መቀጫው እንዲነሳ፣ 3. እንዲሁም ፍሬ ግብሩን በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችሉ ግብር ከፋዮች የክፍያ ስምምነት ውስጥ በመግባት በመመሪያው መሠረት የታክስ ዕዳቸውን በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ፣ ጉዳዩ በዚሁ መሠረት መፍትሔ እንዲሰጠው የተወሰነ መሆኑን በመግለፅ ከዚህ ቀደም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በ17/4/2016 ዓ.ም በቁጥር ታፖመ/ነ/620/16 የተፃፈው ደብዳቤ በዚህ የተተካ መሆኑን አሳስቧል፡፡

❤21👍2🙏2
December 5, 2025 17K 84