Crypot ውስጥ Pumping Crypto የተባለ system አለ ምድነው ለምን ይጠቅማል? pumping… — Hulu crypto — TG.ME

Forwarded fromIBIbro markets
Crypot ውስጥ Pumping Crypto የተባለ system አለ ምድነው ለምን ይጠቅማል?

pumping crypto ማለት  ትሬደሮች ወይም በባለሀብቶች ቡድን የተቀናጁ የ crypto ዋጋን በሰው ሰራሽ መንገድ ማለትም እራሳቸው የተቀናጁት ሰዎች የሚጨምሩበትን መንገድ ነው።

የፓምፑ ዋና ግብ ፍላጎት መጨመር, ሌሎች የcrypto market ተሳታፊዎችን መሳብ እና ከዚያም ክሪብቶዎቹን በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ ነው ይህ ሂደት ብዙ ጊዜ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪን እና ማሽቆልቆሉን ያስከትላል ይህም ልምድ ለሌላቸው ባለሀብቶች ኪሳራ ሊያደርስ ይችላል።

pumping እንዴት ይሠራል?

1ኛ ቡድን ማደራጀት፡ ተሳታፊዎች የአንድ የተወሰነ cryptocurrency ግዢ በተቀናጀ መልኩ በእኩል ሰዐት ለመግዛት  ይስማማሉ ብዙ ጊዜ በግል ቻቶች ወይም የራሳቸውን ግሩፕ ከፍተው መቼ እና ምን crypto ላይ invest እንደሚያረጉ ይመካከራሉ።

2ተኛ የዋጋ ጭማሪ፡ ክሪብቶው በቡድን  በመግዛት ሌሎች ትሬደሮች ድንገተኛ ፍላጎት ይፈጠርባቸዋል ይህም ዋጋውን ከፍ ያደርገዋል

3ተኛ ሌሎች ትሬደሮችን መሳብ፡- የዋጋ ጭማሪው አዳዲስ ትሬደሮችን በመሳብ ትርፋማነትን የበለጠ ያሳድጋል

4ተኛ crypton መሸጥ፡- ዋጋው ሲጨምር  ይህን እቅድ ያቀዱት ሰዎች ወዲያው የገዙትን ክሪብቶ ይሸጣሉ በዚም ትልቅ ትርፍ ያገኙበታል!

pumping ጉዳቱ

unpredictability፡ ዋጋው በማንኛውም ጊዜ crash ሊያረግ ይችላል።

market manipulation:- ፓምፕ ማድረግ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነና ካቀዱት ሰዎች ውጪ ሌሎች ሰዎችን ለኪሳራ ሊጥል ይችላል በአንዳንድ አገሮች ሕገወጥ ነው።

ኪሳራ፡- ዘግይተው trade ያረጉ ሰዎች ብዙ  ገንዘባቸውን ያጣሉ ዋጋው መጨመሩን እና ብዙ ሰው invest እንዳደረገበት ብቻ ነው ሚያዩት ከጀርባ በምን የተነሳ እንደጨመረ ምንም የሚያቁት ነገር ስለሌ ለኪሳራ ይጋለጣሉ።
🔥3
April 3, 2026 102