#Update #MoE
" እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር
ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ከ የካቲት 27/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ማታ 12፡00 ሰዓት ድረሰ ብቻ እንደሚከናወን የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ዛሬ በሚያበቃው የአመልካቾች የምዝገባ ሂደት ለመመዝገብ የሞከሩ ተፈታኞች የመመዝገቢያው ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ እየሰራ አይደለም የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጣቸው ስልኮች ቢኖሩም እየሰሩ አለመሆኑንም ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዶ/ር ኤባ ሚጀናን ማብራሪያ ጠይቋል።
በምላሻቸውም " የኔትወርክ ችግር ይሆናል እንጂ ሲስተሙ ይሰራል ደጋግማቹ ሞክሩ " ብለዋል።
አክለውም " ሁሉም ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎች ናቸው ለመመዝገብ እክል የገጠማቸው በርካታ ሰዎች አሁንም እየተመዘገቡ ነው " ያሉ ሲሆን እስካሁን ባለው 8 ሺ የሚጠጋ ሰው መመዝገቡን ጠቁመዋል።
" ፕሮሲጀሩን መከተል ግድ ይላል ከዘለሉ ላይሰራ ይችላል ነገር ግን ሁል ጊዜ ብዙ ሰው በመጨረሻ ነው የሚመዘገበው ፣መጨናነቅ ይኖራል እንዳይዘጋ በሚል በርካታ ሰዎች በአንድ ላይ ስለሚሞክሩ ጫና ይኖራል በዚህ ምክንያት ካልሆነ በቀር ምንም ችግር የለበትም " ነው ያሉት።
ሊራዘም የሚችልበት አጋጣሚ ይኖራል ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም " መራዘም ሳይሆን እስከምሽት ድረስ እየሞከሩ መቆየት ይችላሉ ኔትወርክ ያለበት አካባቢ በመሆን ደጋግመው ይሞክሩ " ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተፈታኞች የመፈተኛ 'User Name' እና 'Password' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ መሆኑን እና የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም እንደሚጠበቅባቸው ማስታወቁ ይታወሳል።
ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቀጣይ እንደሚገልጽ አሳውቋል፡፡
መመዝገቢያ ፦ https://ngat.ethernet.edu.et/registration
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Forwarded fromTIKVAH-ETHIOPIA
March 10, 2025 754

