#የውቅያኖስ ወለል ምስጢር፦ የዓለምን ኢንተርኔት የሚያንቀሳቅሱት የባህር ስር መስመሮች❗❗
ብዙዎቻችን በየቀኑ በስልካችን የምንጠቀመው ኢንተርኔት፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት በሳተላይት በኩል በአየር ላይ የሚጓዝ ቢመስለንም፣ እውነታው ግን ከዚህ እጅግ የራቀ ነው።
የዓለማችን 99 በመቶ የሚያህለው የኢንተርኔት ዳታ የሚጓዘው በጨለማውና በጥቁሩ የውቅያኖሶች ወለል ላይ በተዘረጉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች በኩል ነው። በዓለም ዙሪያ በውቅያኖሶች ስር የተዘረጉት እነዚህ ከ550 በላይ ንቁ ካብሎች ከ1.4 ሚሊዮን ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን፣ በሴኮንድ በመቶ ቴራባይት የሚቆጥር ዳታ የሚያስተላልፉት እነዚህ መስመሮች እንደተጠበቀው ትልቅ ሳይሆኑ የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያ ወይም የጓሮ ቧንቧ ያህል ውፍረት ብቻ ያላቸው ናቸው።
በኬብሉ መሃል የሚገኙት የመረጃ ማስተላለፊያ የብርጭቆ ጫፎች ወይም ቀጫጭን የብርጭቆ ገመዶች የሰው ፀጉር ያህል ቀጫጭን ሲሆኑ፣ መረጃን በብርሃን ፍጥነት ያጓጉዛሉ።እነዚህ መስመሮች ለአደጋ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በየዓመቱ በአማካይ ከ100 በላይ የመቆረጥ አደጋዎች ያጋጥሟቸዋል ተብሏል።
የመርከብ መልሕቆች መሬት ሲቧጥጡ፣ የባህር ስር የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ወይም አልፎ አልፎ የሻርክ አሳዎች ሲነክሷቸው መስመሮቹ የሚበጠሱ ሲሆን፣ አንድ የባህር ስር ኬብል ከተቋረጠ የሙሉ ሀገር ወይም ቀጠና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ወይም ሊዘገይ ይችላል ነው የተባለው።
በአሁኑ ወቅት እንደ Google፣ Meta፣ Microsoft እና Amazon ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የራሳቸውን የባህር ስር ኬብሎች በመዘርጋት የዓለምን የመረጃ መረብ በባለቤትነት እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።
https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23
Forwarded fromEthio - ዜና 🇪🇹
2July 23, 2026 202




