ነሐሴ 18/2018 ዓ/ም
በጉራጌ ዞን የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ክህሎት መር የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ስራ እድል ፈጠራ ለማህበራዊ እና ለኢኮኖሚያዊ እድገት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በዘርፉ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በጉራጌ ዞንም ባለፉት 3 አመታት ውስጥ 23 ሺ 318 ዜጎች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ስልጠና ተሰጥቷል።
ህገ ወጥ ደላሎችን በመከላከል ፣የዜጎች ደህንነት በመጠበቅ፣ ህጋዊ የስራ ስምሪት መስመሮችን ለማጠናከር እና ፍትሀዊ ጥቅም እንዲያገኙ ጉልህ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።
በጉራጌ ዞን በ2019 በጀት አመት 16ሺ 153 ዜጎች የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ፣የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን፣የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አርሺያ አህመድ፣የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ስርግማ፣የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት አመራሮች፣የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ባለሙያዎችና የኮሌጅ ዲኖች ተገኝተዋል።
August 24, 2026 96