#ተጨማሪ ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም በሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወቅት ተፈታኞች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ-ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተመዛኞች የመረጣችሁትን የፈተና ማዕከል ለማየት፦ https://t.me/M0H_EThiopia/3191 ተመዛኞች ስማችሁ ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ እንደማይፈቀድላችሁ ተገልጿል፡፡ https://t.me/ClinicalPharmacist21
5
1August 12, 2026 1.9K