Update የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን… — Pharmacotherapy®️ Up-to -Date Information 🥼💉💊🩺🔬 — TG.ME

#Update የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዛችሁ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂ ተመዛኞች ከሐምሌ 27- 30/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት Fayda and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ ጤና ሚኒስቴር አሳስቧል። እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር መጠን ገደብ ስለተቀመጠለት የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ https://t.me/ClinicalPharmacist21

❤6👍2
August 3, 2026 2.9K