የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ተመዛኞች በሙሉ ________ የጤና ሚኒስቴር… — Pharmacotherapy®️ Up-to -Date Information 🥼💉💊🩺🔬 — TG.ME

የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ተመዛኞች በሙሉ ________ የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ ጤና ባለሙያዎች በነሀሴ ወር 2018 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመስጠት ተመዛኞች ከሰኔ 30/2018ዓ.ም ጀምሮ መረጃችሁን በማስተሳሰር ላይ እንደምትገኙ ይታወቃል፡፡ ስለዚህም መረጃችሁን ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ማስተሳሰር የምትችሉት እስከ ሃምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን ተገንዝባችሁ ይህንን https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ/Link/ በመጫን የብሄራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (National ID FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ▪ ይህ መረጃን የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡ ▪ በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳስባለን። https://t.me/ClinicalPharmacist21

❤1👍1
July 22, 2026 2.5K