CJ MATH INFO: post #1291 — TG.ME

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፤ 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸው ተገለጸ

የቀድሞው ትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ
ፈተና ከወሰዱ 560,210 ተማሪዎች መካከል 70,544 (12.8%) የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አምጥተዋል። በውጤቱ መሠረት 88
ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ (100%) ሲያሳልፉ፣ በአንጻሩ 585 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ
አላሳለፉም። ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በተመለከተ፦ በተፈጥሮ ሳይንስ ከአዳማ ኦዳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
(591.6) እና ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት (583) ከፍተኛ ውጤት ሲመዘገብ፣ በማኅበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከዶዶላ ኢፋ
ቦሩ (576.2) እና ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር (569.1) ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።

የተማሪዎች የግል ውጤት በመጪው ሰኞ ወይም ማክሰኞ የሚላክ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ ካደረጉ በኋላ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም በፍጥነት ጥሪ እንዲያደርጉ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። ሚኒስቴር መሥሪያ
ቤቱ የ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ምዝገባ ተጠናቆ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀመር አቅዶ
እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
August 22, 2026 27