By Dr. Hawlet Ahemd ''የቁንጅና ውድድር'' ብሎ ነገር አይገባኝም። እና እኔ ስላልገባኝ አገሬ… — Ethiopian Diaspora Civility Forum — TG.ME

By Dr. Hawlet Ahemd ''የቁንጅና ውድድር'' ብሎ ነገር አይገባኝም። እና እኔ ስላልገባኝ አገሬ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ የወከለችና ብርቱ ፉክክር የሚጠብቃትን ልጅ ድምጽ ልንፈጋት? ከፍዬ ሁላ ነው ብዙ ድምጽ የሰጠኋት! የአገራችንን ሥም በመልካም የሚያስጠሩ ነገሮች እየተመናመኑ ነው። በዓለም መድረክ የምናንጸባርቅበት አትሌቲክስ ከሸፈተ ሰነባበተ። የመጨረሻውን ኦሊምፒክ በአንዲት የወርቅ ሜዳልያ ብቻ ማጠናቀቃችንን እናስታውስ። በእርግጥ በዓለም በብዛትም በጥራትም ልንደምቅ የምንችልባቸውን መድረኮች ማስፋት ለሁላችንም የተሰጠ የቤት ሥራችን መሆኑ መዘንጋት የሌለበት ነው። ሩት ይርጋለም ኢትዮጵያን ወክላ የምትወዳደርበት ''Miss World' በዓለም ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር የሚያስተናግዱ ኩነቶች ''Top 10 list'' ውስጥ የሚገኝ ነው። ይሄ አገራችንን ለማስተዋወቅ ምርጥ አጋጣሚ ነው። ሲጀመር በአገራቸው ሥም እኮ ነው የሚጠሩት። ''Miss Ethiopia!'' ኤርትራዊቷ ስኒት (ሥራሥሯና ሐረጓ ያው የት እንደሆነ ቢታወቅም 😒) ተጽዕኖ ያሳደረችባችሁ ኢትዮጵያውያን ምን ሆናችሁ ነው ግን? ኧረ ተው?! 😄 በቃ ስኒትን እየወደዳችሁ ስትመርጡ ግን አገራችሁን ምረጡ። በዚያ ላይ ከ ''Screen Saver'' ፎቶዋ ውጪ ጉግል ላይ search አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ ስኒት ሩት ላይ አትደርስም! እውነቴን ነው። የኤርትራውያን ዳያስፖራዎችን ተጽዕኖ እንርሳውና ስኒት አሁን ያገኘችው ድምጽ መላው ኤርትራውያንን ሕዝብ ብንወስድ 10% አካባቢ ደርሳለች። ወደ ሩት ስንመጣ ሙሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከወሰድን ለ 0 የተጠጋ ፐርሰንት ነው የምናገኘው። በኢትዮጵያ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር (30,000,000) ብቻ ብንወስድ እንኳን አሁንም ከ 1% በታች ነው። ከኤርትራውያን ድምጽ ሰጪዎች እኩል ብንጓዝ ሩት እስካሁን 13 ሚሊየን ድምጽ ማግኘት ነበረባት። ሒሳቡን እንተወው! ድምጽ እንስጥ ጓዶች! ለአገራችን ድምጽ እንስጥ! https://missworld.1voting.com/en/candidate/EVENT_dNWcJ/ethiopia-Fczj?fbclid=Iwb21leAT7Z6NjbGNrBPtnn3Bkb2YFZXh0bgNhZW0CMTEAc3J0YwZhcHBfaWQMMzUwNjg1NTMxNzI4AAEeHBolMNRvPr_iD5Y4pFF5bGwzWMotjdDRJJm1D2F5dOO3r82D6FnXocHaOoI_aem_X2cAmYeSh8m8tYLPRrexEQ

August 26, 2026 415 2