ባንካችን ለአ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ ለአ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመማሪያ ክፍሎች ዕድሳት የሚውል የ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
የባንካችን የዋና ስራ አስፈጻሚ ኤክስኪዩቲቭ አሲስታንት የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤት ገብሩ ዛሬ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የኮሌጁ የ1993 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የ25ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን ባከበሩበት ዝግጅት ላይ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል።
ወ/ሮ ኤልሳቤት ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ እንደተናገሩት ይህ ድጋፍ ባንካችን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ከመሆኑም በላይ፣ ለመማር ማስተማር እና ለዘላቂ የማኅበረሰብ ዕድገት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የአ.አ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ድጋፉን የተረከቡት የኢንዳውመንት ፈንድ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሪት ሰማያዊት ባህሩ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ በዩኒቨርሲቲው ስም አመስግነዋል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የአ.አ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው የሥራ ሐላፊዎች፣ የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ባንካችን ባለፈው ዓመት እ.ኤ.አ በ2025 ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀንን በማስመልከት ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው መርሐ ግብር ላይም በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ብር 400,000.00 የሚገመት የዊልቸርና የመቅረጸ ድምፅ መሣሪያዎችድጋፍ አድርጎ ነበር።
57
16
12August 29, 2026 9.8K 3






