Bahir Dar Institute of Technology: post #2360 — TG.ME

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የኬሚካል እና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ :-
1ኛ. በመደበኛው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤
2ኛ. በማታው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤
ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከነሀሴ 11/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች የሚያመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ (https://bdu.edu.et/registrar/?fbclid=IwcGRvZgFleHRuA2FlbQIxMABicmlkETFDblc2UW9jVkY0OG1EU0tLc3J0YwZhcHBfaWQQMjIyMDM5MTc4ODIwMDg5MgABHg9acYEHklgwVRutUZBqhelLuOsZIJUVBYJZeEny4BMyeSbYiet97wBvRaS5_aem_12uuQ0NT7MGw69e5yS1HWQ) ወይም ከዚህ በታች ከተያያዘው ፖስተር መመልከት የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፣
• የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤
• ኦፊሻል ትራንስክርፕት
• በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
• የ National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያለው/ያላት፣
• ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር
1000013094563 ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (BiT) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ
የማመልከቻ ቦታ፤
• ምዝገባ የሚካሄደው በ “Online” በድህረ ገጽ http://studentportal.bdu.edu.et/ (http://studentportal.bdu.edu.et/?fbclid=IwcGRvZgFleHRuA2FlbQIxMABicmlkETFDblc2UW9jVkY0OG1EU0tLc3J0YwZhcHBfaWQQMjIyMDM5MTc4ODIwMDg5MgABHg9acYEHklgwVRutUZBqhelLuOsZIJUVBYJZeEny4BMyeSbYiet97wBvRaS5_aem_12uuQ0NT7MGw69e5yS1HWQ) በመጠቀም ወይንም በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (BiT) ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የኬሚካል እና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ፣ ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
August 24, 2026 193