📍 masculine
|
|
1. Toxic masculinity
ደደብ ወንድ
|
ዝንጀሮን ይመስላል። ክፍለ ሀገር ስትሔዱ በአውቶብስ መስኮት ዳቦ ወርውሩለትና እዩት። የልጁን እናት አሽቀንጥሮ ጥሎ ከጨቅላው ነጥቆ ይበላል። ልጥልጥ መሀይም ነው። የሚገርመው ደግሞ በDna በጣም ለኛ የሚቀርበው እንስሳ መሆኑ ነው።
|
|
ዝንጀሮ ወጠጤነቱ ሲያገግም፤ ጡንቻው ሲፋፋ፤ ብብቱን ሲያልበው ኮቴ ለክቶ ከአባቱ ይደባደባል። አሸንፎ እናቱን ሊበዳ። አትደነቁ! በዘራቸው ከዚህም የሚከፋ የነጠረ ደነዝ አለላችሁ። ይሔ ደሞ ጓደኞቹንም ይማታል። ብብቱ እስከቻለለት ሴት እና ሙዝ ይሰበስባል። የመረራቸው ጓደኞቹ ሲዘናጋ ጠብቀው በደቦ ደብድበው ይገሉታል።
|
|
ደደብ ወንድ(toxic) የምላችሁ የጎላ የዝንጀሮ ባህሪ የሚታይበትን ጨገራም ነው። ከነሱም መሀል ሟቹን ገመሬ የሚመስል። ከሱም የሚከፋ! ልጁን የሚነፋ ዝንጀሮ መኖሩን መረጃ የለኝም! የሰው ግን አለ። ለማማከር እየዘገነነኝ የማወራቸው ተደፋሪ ሴቶች አሉ። ሰውነቷ ደንግጦ የበደነባት ሴት አቅፌ ተኝቻለሁ🙂↕️
.
|
|
ሚስቱን የሚያጮል ጓደኛ ነበረኝ። ነፍሱን ይማረው። አጭር ናት አሟሟቱ። የደበረው ሰውዬ ገጠመው። እንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ተቃራኒ ቡድን ደገፉ። ጓደኛዬ ላይ ጎል ገባ። ያኛው ሲዘል ይሔኛው ተከለለ። ሟቹ ጓዴ ቡድኔ ላይ ሲገባብኝ over ደስ አለው ብሎ ሰደበው።
|
|
"እናትን ብዳ ቁጭ በል "
ጎረቤቱ ነው። ብቻውን የሚኖር የከፋው ሰው ነው። ቢረዳው አሪፍ ነበር። ሰው ገላገላቸው። ጓዴ ሰፈር ሰላም ብሎ ድድ እያሰጣ ሳለ የዛገ ሽጉጥ ተመዘዘበት። ደም እንዳይፈናጠርባቸው ጓደኞቹን ወደ ቤት አሰናብቶ 4 ቆጠረበት። ገዳዩ ታሰረ ሟቹም ተቀበረ።
|
|
ሁላችን ስንወለድ አልቃሻ ነንና እናስጠላለን። ቤተሰቦቻችን ይማረራሉ! አባብሎ ብቻ ሳይሆን አፋችንን ብሎ ዝም ማሰኘት ያምራቸዋል። በወጉ ተቀጥተው በለቅሶ ሁሉን ማግኘት እንደማይቻል የገባቸው በስርአት ያድጋሉ። ያዘነ እየመሰለ ቀልብ የሸቀለስ? ሲያድጉ ሁሌ ታማሚ፤ ቋሚ ተደባሪ፤ ምን ሆንክ ተባይ፤ አኩራፊ ይሆናሉ። ማልቀሱን ወደ መመናጨቅ እና እቃ መወርወር ሲያሳድግ በጡት በአሻንጉሊት ዝም እንዲል ከተደረገ ጓዴን ሆነ። ከፍ ብሎም በጡንቻው እና በቁጣው መንጠቅ ይፈልጋል። በሁለተኛው መንገድ የሔዱ እንደ ጓዴ ሞተዋል ወይም እንደገዳዩ እስር ቤት።
|
|
2. masculine
ወንድ
|
|
ይሔ ባህሉ ውስጥ ውድ የተባሉትን ነገሮች ታግሎ በፍትሀዊነት ለማግኘት የሚያለከልክ ነው። ማለክለክ ላይሳካለት ያልኩት ሊሳካለትም ስለሚችል ነው። በላቡ በወዙ የሚበላና የሚያርፍ ጥቂት ነው። ቆንጀ ሚስት፣ ታዋቂነት፣ ገንዘብ፣ ልጆች፣ ስርአት እጥረት አለብን። በጤናማ ዘመን ከተገኘ በብዙ ጥረት ይሳካለታል። ሽክ ይላል። ሲራመድ ደረቱን ከቦርጩ ያስቀድማል። ከስኬቱ ጀርባ ያገኘውን ባዶነት ደብቆ ፏ ማለት ይችላል። እኔ የሚለው የሚያስቀድሰው Ego እዚህ ጫፍ ላይ ሊከነበል እና 3ኛውን ወንድ ሆነው ሊነቁ ይችሉ ነበር። በተቃራኒውም የሔዱት ወለሉን ነክተው Egoአቸው ሊፈርስ እና ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ።
[ ባይገናኝም ጥበብ ወደሁለቱም ሳይሔዱ ወደሶስተኛው መፈናጠሪያ የማርያም በር ትከፍታለች]
|
|
📍#ዊልስሚዝ ክሪስ ሮክን ጥፊ ሲያልሰው አለም ጮኧ። ዊልስሚዝ ግን masculine እንጂ toxic ሆኖ አልነበረም። ሚስቱን ነው የተከላከለው። ሚስትቱ ስትሰደብ ፈገግ የሚል ሴት አይደለምን? እርሱ ሲሰደብ አለመናደድ አንድ ነገር ነው። ጥቃት ቆዳ ላይ ብቻ ነው የሚያርፈው? ጆሮ ላይም አያርፍም? አፍንጫ ላይም ማረፍ ይችላል በፈስ። ማነው ከህዋሶቼ መሀል ቆዳዬን ለይቶ ቆዳህ እስኪነካ ታገስ የሚለኝ! እኔ ቆዳዬ ጫፍ ላይ አበቃለሁ?
|
|
አለም በዊል ስም ወንድነትን አውግዛለች። "በወላቃ እናትህ ጥርስ ስቀልድ ፈገግ በል! Egoህን አታንጫጫ! እፊቷም ቢሆን የተቀለደው እንደ ደበራት እያየህም ፈታ በል"
ትላለች።
.
ወንድ አውሬ መሆን አለበት። ሲችል ባህሉን የሚጠብቅ፤ ካልተቻለም ቅጥሩን አጥብቦ ቤቱን የሚከላከል። ይሔ ወንድ በምስጢር እንጂ በግልጽ አይፈለግም።
(ይሔ አይነት ካለህ እንደ ማርያም በልብህ ጠብቀው)
.
የሚለማመጥ፣ እኔ ብሎ ማውራት የሚደብረው፤ ሁሉም እንደየአመለካከቱ ነው እያለ እውነትን የሚሸሽ እምስ እንጂ ቁላ አይደለም። ከፈርኦን ቤት ያደገውን ሙሴን ይመስላል። ሙሴ እስራኤላዊ ሲጎዳ አይቶ ግብጻዊ ገደለ። ፈርኦን ይሔን አይፈለግም። ተሳዶ በረሀ ገባ። የሱ ምቾት ስላልጎደለበት አርፎ መኖር ነበረበት? ይሔ ወንድ አሁንም ቢሆን አይፈለግም።
.
ተመስገን ደሳለኝ፤ ዘመነ ካሴ፤ አሳምነው ጽጌ፤ በላይ ዘለቀ በዚህ ያልፋሉ!
|
|
3. Divine masculinity
መለኮታዊ ወንድ!
|
ስለዚህ ብዙ ብያለሁ በተደጋጋሚ ሊንክ ከፈለጋችሁ አጣብቃለሁ። ይሔ አንበሳን ይመስላል። ይሔ ኢየሱስን ይመስላል። ይሔ አውሬነቱን የገራ ኖህ ነው። ያለሞት አይገኝም ይላሉ። እዚህ ለመድረስ ሙሉ ለሙሉ የመጀመርያውን ወንድነት መጣለሰ አለበት። የሚጥለው ግን ወርውሮ አይደለም። አባቱ እግር ስር መሆን አለበት። ይስሀቅ አባታችን ደግሞ ወንድ ይወዳል። ተንበርክኮ እግሩን የሚስመው አዳኝ ልጁን ነው። ወንድ መስሎ ወንድን መሸወድ የቻለ እርሱ የተነሳ ወንድ ይሆናል።
|
|
#መለኮታዊ_ወንድ ለስልጣን አይሮጥም። ከጡንቻው ይልቅ በመንፈሱ ይመራል። አይኑን እና አፉን አልፎ ለመጠጋት የሚቸግር ሞገስ አለው። ጡንቻው ይሔን ማለፍ ለቻለ እውር የሚሰነዘር እንጂ መታመኛው አይደለም። በደግነት ስም አይሸወድም እንደ #psychopath ያስባል። ሰውነት በውሸት እና በስርቆት የሚንቀጠቀጥ ከሆነ በእውነት ይገነባልና ሰውነቱ የቆመበት እውነት አለና ይቀርቡት ዘንድ ያስፈራል።
.
ታሪካቸውን ከማውቃቸው የተነሱ ወንዶች መሀል ምኒሊክ!
62
9
3
3
2
1June 26, 2026 4.1K 16